ነገ በአዲስ አበባ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።
በትግራይ ክልል እየተባባሰ የመጣውን ቀውስ ለመቃወምና ለማስቆም እንዲሁም ለፌደራል መንግስትና ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ለማሳወቅ ''አፈሳ ይቁም ሰላም ይስፈን'' በሚል መሪ ቃል ሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ/ም ከጥዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፉ ይደረጋል።
ሰልፉ ተጀምሮ እስከ ሚጠናቀቅበት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።
በዚህም መሰረት:-
* ከመገናኛ በ22 አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ቅ/ዑራኤል አደባባይ
* በቦሌ መንገድ ወደ መስቀል አደባባ ኦሎምፒያ አደባባይ
* ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ መስቀለኛ ለቀላል ተሽከርካሪ ጥላሁን አደባባይ
* ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ መስቀል ለገሀር መብራት
* ከለገሀር ቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታዲዮም ለገሀር ቴሌ ማቋረጫ
* ከአራት ኪሎ ወደ መሰቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ-መንግስት
* ከካሳንቺስ በመቅረዝ ሆስፒታል ወደ መስቀል አደባባይ መቅረዝ ሆስፒታል አጠገብ
* ከአምባሳደር ቴአትር ወደ መሰቀል አደባባይ ሐራምቤ መብራት የሚወስዱ መንገዶች ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።
ከዛሬ ሐምሌ 10 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ በመስቀል አደባባይና በዙሪያው ባሉ መንገዶች ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ተሽከርካሪ ለአጭርም ሆነ ረዥም ሠዓት ማቆም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።
ለተጨማሪ መረጃ፡- https://linktr.ee/Addis_Ababa_Communication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.