"ምከር ቤቱ ለህዝብ ተጠቃሚነት፣ ለዲሞክራሲያዊ ስርዓትና ለሃገር ግንባታ ወሳኝ መሆኑን በ 5 ዓመታት ቆይታ በተጨባጭ ማረጋገጥ ችሏል፡፡" ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ከንቲባዋ ይህን ያሉት በም/ቤቱ 2ኛ ቀን ጉባዔ የቀረበዉን የም/ቤቱን የ 5 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት መነሻ በማድረግ ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነዉ፡፡
የአዲስ አበባ ምክር ቤት ባለፉት 5 ዓመታት የህዝብን አደራ እና ኃላፊነት በተገቢዉ ሲወጣ መቆየቱን የጠቀሱት ከንቲባ አዳነችአቤቤ የምክር ቤቱ ግምገማዎች እና የግምገማ ዉጤቶች ለከተማ አስተዳደሩ ግብዓት በመሆን ታላላቅ ስኬቶች በከተማዋ እንዲመዘገቡ የላቀ አስተዋፅኦ እንደነበረዉ ገልፀዋል፡፡
አያይዘዉም ከማከል እስከ ታችኛዉ መዋቅር ድረስ በአካል በመገኘት ፤ጠንካራ ክትትል እና ቁጥጥር በማድረግ የአመራሩ እና የተቋማት አፈፃፀም ዉጤታማ እንዲሆን አስችሏል ብለዋል ፡፡
የምዘና ዉጤቶቻችን የእዉቅና ስርዓቶችም አንዱ የምክር ቤቱ የስራ ዉጤት ማሳያዎች ናቸዉ ሲሉ አክለዉ ገልፀዋል፡፡
በኦዲት ግንቶች ላይ ማስተካከያ እንዲደረግ ከማድረግ ባሻገር የአሰራር ተጋላጭነትን ለማስቀረት እንዲሁም ተጠቂነትን እንዲሰፍን ለማድረግ የተመራበት አግባብ ጠንካራ እንደነበረና ይህም የበለጠ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም የህዝብ ልሳን በመሆን ህዝቡ ለሚያነሳቸዉ ጥያቆዎች ትኩረት በመስጥት በአፈፃፀማቸዉ ዙሪያ ጭምር ትክክለኛ መረጃ ተደራሽ እንዲሆን የሚዲያ አካላት የበኩላቸዉን ሚ,ና እንዲወጡ ም/ቤቱ ያደረገዉ ጥረት የላቀ ነዉም ብለዋል፡፡
በሌላ በኩልም ምከር ቤቱ ለህዝብ ተጠቃሚነት፤ለዲሞክራሲያዊ ስርዓትና ለሃገር ግንባታ ወሳኝ መሆኑን በ 5 ዓመታት ቆይታ በተጨባጭ ማረጋገጥ በመቻሉ ለቀጣይ በበለጠ ማጠናከር ይገባልም ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ከቋሚ ኮሚቴዉ ባለፈ እስከ ባለሙያዉ ድረስ በእዉቀት የታገዘ ጠንካራ የክትትል እና የቁጥጥር ስርዓት በመዘርጋት ሳይንሳዊ ትንታኔዎችን በተጨባጭ በመተግበር ለሁለተናዊ ለዉጥ በቅንጅት ተግቶ መስራትም አንዱ የትኩረት አቅጣጫ መሆን እንዳለበት ከንቲባ አዳነች በምላሻቸዉ ገልፀዉ ልባዊና የላቀ ምስጋናቸዉን ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.