የከተማችን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ሁለተኛ ቀን ውሎ በማካሄድ ላይ እንገኛለን ።
በዛሬ ማለዳው ክፍለ ጊዜ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ5 ዓመት የህግ ማውጣት ሚና፣ የህዝብ ውክልና አፈፃፀም፣ የአስፈፃሚ አካላት ክትትልና ቁጥጥር አፈጻጸም ሪፖርትና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ተወያይተን አፅድቀናል።
በአሁኑ ሰአት የከተማችን ዋና ኦዲተር 107 የከተማዋ ተቋማት ላይ ያዘጋጀው ሪፓርት እየቀረበ ነው ። ውድ የከተማችን ነዋሪዎች ሁሉም አጀንዳዎች በአዲስ ሚድያ ኔትዎርክ ስርጭት እየተላለፈ ስለሆነ መከታተል ትችላላችሁ
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.