ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ሰፋ ያሉ ማብራሪያ እና ምላሽ
የከተማዋን የጎርፍ ተጋላጭነትን ከግምት ዉስጥ በማስገባት ቅድሚያ አቅደን የለየናቸዉና የማቅለያ እርምጃ የተወሰደባቸዉ ስራዎች የተከናወኑ እና እየተከናወኑ ያሉ ሲሆን ይህም በአንድ ወቅት ብቻ ሳይሆን በዘላቂነት መፍትሄ እየተሰጠበት የሚሰራ የህዝባችንን እና የተቋማት ቅንጅት የሚሻ ቀዳሚ ተግባር ነዉ፡፡
በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ
አስራ አንድ የአንድ የመሶብ ማእከላት ከ150 በላይ ዲጂታላይዜድ አገልግሎቶች እየተሰጡ በመሆኑ ብልሹ አሰራርን ከማስቀረት፤ተጠያቂነትን ከማስፈን ባሻገር ፈጣን እና ጥራት ያለዉ አገልግሎት መስጠት መቻሉ እና ከዚህ ጋር ተያይዞም የተቋማት የሪፎርም ስራዉ የተፈለገዉን ዉጤት ለማምጣት የበኩሉን አስተዋፅኦ እያደረገ ስለሚገኝ ተጠናክረዉ የሚቀጥሉ ተግባራት ይሆናሉ፡፡
በም/ከንቲባ ማእረግየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጀማሉ ጀምበሩ
በከተማችን የመስሪያ ቦታዎች ደረጃቸዉን የጠበቁ እንዲሆኑ ትኩረት ተሰጥቶ በመሰራቱ ባለፉት አምስት ዓመታት ለ2.2 ሚሊየን የሚጠጉ ዜጎች የስራ እድል በመፍጠር ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለ ሲሆን በቀጣይም በማኒፋክቸሪንግ፤ በግብርና፤ በኮንስትራክሽን እና በአገልግሎት ዘርፎች ላይ የተጀመሩ ስራዎች የበለጠ ተጠናክረዉ የሚቀጥሉ ይሆናል፡፡
በም/ ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ እና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ
ከገቢ ጉዳዮች፤ከከተማ አስተዳደሩ ካሽ አለቃቀቅ እና ከፌደራል በጀት ድጎማ ጋር በተያያዘ ምላሽ የሰጡ ሲሆን በተለይም ከተማችን ባለፉት ዓመታት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የልማት እቅድን ለማሳካት በራስ አቅም ተቋማትን ሪፎርም በማድረግ፤አሰራርን በማዘመን እና ተጠያቂነትን በማስፈን በመሰረታዊነት የገቢና የወጪ እሳቤን ማጎልበት በመቻሉ የከተማዋ ገቢ ከ2013 ከነበረበት 51 ቢሊዮን ወደ 350 ቢሊዮን በሰባት እጥፍ ማሳደግ ተችሏል፡፡
በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን
“ባለፉት አምስት ዓመታት በታቀደው ልክ በርካታ ለውጦች ተመዝግበዋል” ፡- አቶ ጃንጥራር አባይ
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ፤ ባለፉት አምስት ዓመታት በታቀደው ልክ በርካታ ለውጦች መመዝገባቸውን ገለጹ።
ኃላፊው እንደሚያስረዱት ቀደም ሲል በነበሩ የፍትሐብሔር ጉዳዮች የፍርድ ቤት ክርክሮች ላይ መንግሥት የሚረታባቸው ሂደቶች ተቀይረው በአሁኑ ወቅት የመንግሥትና የሕዝብ ሀብትን እንዲሁም ጥቅምን ማስከበር ሰፊ ለውጦች ተመዝግበዋል።
ከተማ አስተዳደሩ በትራንስፖርት፣ በጤና መድህን፣ በተማሪዎች ምገባና በሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቶች ላይ እያደረገ ያለው ድጎማ የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ አዎንታዊ ድርሻ እንደነበረውም አብራርተዋል።
በተጨማሪም የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት የገበያ ማዕከላትንና የሰንበት ገበያዎችን በማስፋት፣ ነዋሪው በአቅራቢያው የግብይት አገልግሎት የሚያገኝበት የአሠራር ሥርዓት መዘርጋቱን አቶ ጃንጥራር ጠቁመዋል።
በመካከለኛው ምሥራቅ ከተከሰተው ግጭትና ከነዳጅ አቅርቦት ጋር ተያይዞ በምግብ ዘይት ምርት ላይ ሊከሰት የነበረውን የዋጋ ንረት መንግሥት ድጎማ በማድረግ እንዳይጨምር ማድረጉንና በመሠረታዊ የፍጆታ ምርቶች ላይም ሰፊ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት መከላከሉን አስገንዝበዋል።
በመጨረሻም በዘላቂነት የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ አስታውቀዋል፡፡
ዛሬ ባካሄድነው የከተማችን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ለምክር ቤቱ ያቀረብነዉ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ሰፋ ያሉ ማብራሪያ እና ምላሽ በመስጠት፣ የቀረበው ሪፖርት በሙሉ ድምፅ ፀድቆ የመጀመሪያ ቀን ውሎአችንን አጠናቀናል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.