የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የ2...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የ2018 ዓ.ም ሪፖርት እና የ2019 ዋና ዋና አቅጣጫዎችን ለከተማው ምክር ቤት እያቀረቡ ይገኛሉ።

የኑሮ ውድነትን በተመለከተ

 

የኅብረተሰቡን የኑሮ ጫና ለማቃለልና የምርት አቅርቦትን ለማሳደግ 259 የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ተስፋፍተዋል። 

 

በተጨማሪም በ15.9 ቢሊዮን ብር ወጪ መጋዘኖችን፣ የጅምላና የችርቻሮ ሱቆችን ያካተቱ 7 ዘመናዊ የግብርና ምርቶች መሸጫ ማዕከላት በከተማዋ መግቢያዎች ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል። ቢሮክራሲን በመቀነስም ከ270 ሺህ በላይ አዳዲስ ነጋዴዎች ወደ ንግድ ሥርዓቱ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል።

 

በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ጫና ለማቃለል ለትራንስፖርት፣ ለጤና መድህን፣ ለተማሪዎች ምገባና ለዳቦ ምርት 18.2 ቢሊዮን ብር የመንግስት ድጎማ ተደርጓል። 

 

በተጨማሪም ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ መነሻ ካፒታል ያለው የንግድ ኮርፖሬሽን ሲቋቋም፤ መሠረታዊ የፍጆታ ሸቀጦች በተለይም ስኳር እና የምግብ ዘይት በፍትሃዊነት እንዲሰራጩ ተከናውኗል። አቅርቦትን ለማጠናከርም ለ11 ዩኒየኖች የ825 ሚሊዮን ብር የተዘዋዋሪ ብድር ፈንድ ተሰጥቷል።

ህጋዊነትን ለማረጋገጥ በተደረገ ቁጥጥር ህገ-ወጥ በነበሩ 24,568 የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ ሲወሰድ፣ 20,617ቱ ወደ ህጋዊነት ተመልሰዋል። 

 

በሌላ በኩል አዲስ አበባን አምራች ለማድረግ በተሰራው የከተማ ግብርና እና የሌማት ትሩፋት ስራ 1.2 ሚሊዮን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ሆነዋል። እንዲሁም ከይዞታቸው ለተፈናቀሉ አርሶ አደሮች 19,507 የይዞታ ማረጋገጫ ካርታዎች በመስጠትና ወደ ኢንቨስትመንት እንዲገቡ በማድረግ ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ ተከናውኗል።

 

ባህላዊ፣ ኪነ ጥበባዊ፣ ታሪካዊ እና ተፈጥሮአዊ ሀብቶችን መጠበቅና ማሳደግ በሚመለከት

 

ብሔራዊ አንድነትና የጋራ ትርክት ከመገንባት፣የሀገርን መልካም ገጽታ ለመገንባት፣ የሕዝቦችን አንድነት፣ አብሮነትና ወንድማማችነት የሚያጠናክሩ በርካታ ስኬታማ ሥራዎች ተከናውነዋል።

 

የባህልና እሴቶች ጥበቃ ስራ ጋር ተያይዞ ፡ ባህላዊ እሴቶችንና አገር በቀል ዕውቀቶችን ለማሳደግ፣ እንዲሁም ጎጂ ልማዶችንና መጤ ባህሎችን ለመከላከል 6 የቶክሾው ውይይቶችና በርካታ የስልጠና ስርፀቶች ተካሂደዋል።

 

የጀግኖች መታሰቢያ ስራችን በተመለከተ፡ በሀገርና በትውልድ ግንባታ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የኪነጥበብ ሰዎችና የሀገር ኩራት ለሆኑ አትሌቶች የክብር ሐውልት ቆሟል።

የኪነጥበብ መሠረተ ልማት፡ ቲያትርና ሲኒማን ለማሳደግ ዘመናዊ መሣሪያዎች የተሟሉላቸው እጅግ ዘመናዊ ኮምፕሌክሶች ተገንብተዋል። ጥበብን ለሕዝብ ከማቅረብ አኳያ፡ ኪነጥበብ ወደ ሕዝብ ይበልጥ እንዲጠጋ ለማድረግ በርካታ አንፊ ቲያትሮችና የሕዝብ ፕላዛዎች በሰፊው ተገንብተው ለአገልግሎት በቅተዋል።

ወጣቶችና ስፖርትን በተመለከተ

 

በመዲናዋ በ114 የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት አገልግሎቶችን እንዲሰጡና አገልግሎቶች እንዲያሻሽሉ በማድረግ ወጣቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል። 

 

በባለፉት አምስት አመታት የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ቁጥራቸው 495 የነበረ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት 2,581 ማድረስ ተችሏል፡፡

ከ84,678 በላይ ታዳጊ ወጣቶች በከተማ አቀፍ ስልጠና ልማት ፕሮግራም በማሰልጠን 723 ተተኪና ምርጥ ስፖርተኞችን ለብሄራዊ ቡድን እና ለክለብ የማፍራት ስራ ተሰርቷል።

 

በሌላ በኩል ከ211,213 በላይ ወጣቶች የማይንድሴትና በ225,222 በላይ ወጣቶች የህይወት ክህሎት ስልጠና እንዲሰለጥኑ ለማድረግ ተችሏል ያሉ ሲሆን በበጀት አመቱም ደረጃቸውን የጠበቁ 91 የስፖርት ማዘወተሪያ ስፍራዎችን፣ ስፖርት ፓርክን፣ ለብሔራዊ ጀግኖች ለሆኑ አትሌቶቻችን የአክብሮት አውልት ማቆምን ጨምሮ ብዙ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡

 

በተጨማሪም በየደረጃው የማህበረሰብ አቀፍ ስፖርትን በትምህርት ቤት፤ በመኖሪያ እና መዝናኛ ቦታዎች እንዲሁም በስራ ቦታዎች በማስፋፋት ሁሉንም ዜጎች በአካል እና በአእምሮ ጎልብተው ጤናማ እና አምራች እንዲሆኑ እና ማህበራዊ መስተጋብርን ለማጠናከር ያለማቋረጥ እየተሰራ ሲሆን በአገራችንም ሆነ በከተማ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ 5 አለም አቀፍ ውድድሮችን በማስተናገድ ከተማችንን የአለም አቀፍ ውድድሮች መዳረሻ ማድረግ ተተችሏ::

ገቢን በተመለከተ

 

ባለፉት አምስት ዓመታት የገቢ መሰረትን በማስፋትና አዳዲስ ግብር ከፋዮችን በማካተት የከተማዋን ገቢ በ2013 ከነበረበት 51 ቢሊዮን ብር በ2018 ወደ 350 ቢሊዮን ብር ማሳደግ ተችሏል። የ2018 የገቢ አሰባሰብ ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ50 በመቶ (116.3 ቢሊዮን ብር) ዕድገት አሳይቷል። በዚህም አዲስ አበባ ከአፍሪካ 6 ከተሞች ቀዳሚ በመሆን ልምዷን ማካፈል ችላለች።

 

የበጀት ድልድል፡- ከዘንድሮው 360.07 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ በጀት ውስጥ 71 በመቶው ለዘላቂ ልማት ሲመደብ፣ 29 በመቶው ለመደበኛ ወጪ ውሏል።

 

ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር፡- በኦዲት ግኝቶች 200 ሚሊዮን ብር ማስመለስ የተቻለ ሲሆን፣ በ61 ተቋማት የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ተተግብሯል። የንብረት አያያዝን በማዘመን 6,815 የመንግስት ሕንጻዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ ከ87 ቢሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ሀብቶች በዘመናዊ መረጃ ቋት ተመዝግበዋል። በተጨማሪም ከተጋነነ የህንጻ ኪራይ ክፍያ 100 ሚሊዮን ብር ተመልሷል።

 

ሀገራዊ አስተዋፅዖ፡- ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ6.6 ቢሊዮን ብር በላይ ሀብት ማሰባሰብ ተችሏል።

የበጎ ፈቃድና ሰው ተኮር ስራዎችን በተመለከተ

 

አዲስ አበባን የሰው ተኮር ስራዎችና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማዕከል ለማድረግ በተከናወኑ ተግባራት ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል። ባለፉት አምስት ዓመታት የአቅመ ደካሞችን ቤት በመገንባት፣ ማዕድ በማጋራት፣ በምገባ እና በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሮች ከ92 ቢሊዮን ብር በላይ ሀብት ማሰባሰብ ተችሏል። በዚህም ከ6 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች ተጠቃሚ ሆነዋል።

 

በፕሮግራሙ ከ46 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶች ተገንብተዋል፤ 30 የምገባ ማዕከላት ተደራጅተው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ። በየዓመቱም እስከ 600 ሺህ ዜጎች ማዕድ ተጋርተዋል። በበጀት ዓመቱ ብቻ በገንዘብ፣ በዓይነትና በጉልበት 28.5 ቢሊዮን ብር በማሰባሰብ 1.8 ሚሊዮን ህዝብን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።የበጎ ፈቃድና ሰው ተኮር ስራዎችን በተመለከተ

አዲስ አበባን የሰው ተኮር ስራዎችና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማዕከል ለማድረግ በተከናወኑ ተግባራት ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል። ባለፉት አምስት ዓመታት የአቅመ ደካሞችን ቤት በመገንባት፣ ማዕድ በማጋራት፣ በምገባ እና በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሮች ከ92 ቢሊዮን ብር በላይ ሀብት ማሰባሰብ ተችሏል። በዚህም ከ6 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች ተጠቃሚ ሆነዋል።

 

በፕሮግራሙ ከ46, ሺህ 411 በላይ የመኖሪያ ቤት  ተገንብቷል።

በወሳኝ ኩነት ዘርፍ የተከናወኑ ዋና ዋና ሥራዎችና ብተመለከተ

 

የአገልግሎት ሥርዓቱን በማዘመን የነዋሪነትና የወሳኝ ኩነት ምዝገባ አገልግሎትን ግልጽ፣ ቀላል፣ ቀልጣፋና ፈጣን በማድረግ በፋይል ክምርና መጥፋት እንዲሁም በብልሹ አሠራር ይስተዋሉ የነበሩ ውስብስብ ችግሮችን መቅረፍ ተችሏል።

 

የምዝገባ ሽፋን ዕድገት ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የከተማዋን የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ሽፋን 62.55% ማድረስ ተችሏል።

 

የዲጂታል መታወቂያ አቅርቦት ከአጠቃላይ የከተማዋ ነዋሪዎች መካከል ከ4 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የነዋሪነት ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት ተሰጥቷል

ፋይዳ መታወቂያ ሥርጭት በተመለከተ ፤ 8.6 ሚሊዮን ዜጎች ብሔራዊ የፋይዳ መታወቂያ እንዲወስዱ ተደርጓል።የልደት ምዝገባ አፈጻጸም ስንመለከት በበጀት ዓመቱ 109,891 ወቅታዊ የልደት ምዝገባዎችን በማከናወን ዕቅዱን 94% ማሳካት ተችሏል። በአጠቃላይ አምስቱ የኩነት ዓይነቶች (ልደት፣ ጋብቻ፣ ፍቺ፣ ሞት እና ጉዲፈቻ) በጥምር 500,363 ምዝገባዎች ተከናውነዋል።

የኢንዱስትሪ ልማት በተመለከተ

 

ባለፉት አምስት ዓመታት ለአምራች ዘርፉ በተሰጠዉ ልዩ ትኩረት የውጪ ንግድን በመተካት (ተኪ ምርትን በማምረት) በኩል 24.2 ሚሊዮን ቶን በማምረት ከፍተኛ አፈጻጸም አሳይቷል፡፡ ይህም አገሪቱ ልታወጣው የነበረውን 8.4 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ለማዳን አስችሏል።

 

በኤክስፖርት ዘርፍም 92,522 ቶን ምርት ለውጭ ገበያ በማቅረብ ዕቅዱን ማሳካት ተችሏል፡፡ የተገኘው የውጭ ምንዛሬ 729 ሚሊዮን ዶላር ሆኖ ተመዝግቧል።

 

ከዚህ በተጨማሪ፣ 2,585 የሚሆኑ አምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅማቸው የተለካ ሲሆን፣ አጠቃላይ ምርታማነታቸው 69.75 % ደርሷል።

 

በበጀት አመቱ ለ 664 ኢንዱስትሪዎች በ3.3 ቢሊዮን ብር 6,667 ማሽኖችን ማቅረብ፣ የምርት አቅም ለማሳደግ ደግፈናል፡፡ በተጨማሪም በመስሪያ ቦታ እና መሬት አቅርቦት ረገድ ለ 210 ኢንዱስትሪዎች ምላሽ መስጠት ተችሏል።

 

እነዚህን የኢንዱስትሪ ውጤታማ ለማድረግም ለ664 የመብራት፣ የመንገድ እና የውሃ መሠረተ-ልማቶች በተሟላ ሁኔታ እንዲያገኙ ተደርጓል። የካፒታል እጥረትም ለመቅረፍ ባደረግነው ጥረትም፣ 3.84 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ብድር ለአምራቾቻችን ማድረስ ችለናል።

 

አምራቾችን ከጥቃቅን ወደ መካከለኛ የማሸጋገር ሥራ 57% ማድረስ የተቻለበት ትኩረት የተሠጠዉ ስራ ነው፡፡

ትራንስፖርትን በተመለከተ፡-

የህዝብ ትራንስፖርት አቅርቦትን ለማሻሻል ባለፉት አምስት ዓመታት 467 አዳዲስ አውቶቡሶች በመገዛታቸው የመንግስት አውቶቡሶች ቁጥር 1,628 ደርሷል። በዚህም የቀን ተሳፋሪዎች ቁጥር ወደ 4.19 ሚሊዮን ከፍ ሲል፤ የብዙሃን ትራንስፖርት ሽፋን ከ9 በመቶ ወደ 41 በመቶ አድጓል። ችግሩን ይበልጥ ለማቃለልም የ500 ተጨማሪ አውቶቡሶች ግዢ በሂደት ላይ ይገኛል።

የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ አገልግሎቶችን በማሻሻል የተሽከርካሪ ምዝገባ፣ የቴክኒክ ምርመራ እና የብቃት ማረጋገጫ አሰጣጥ በከፍተኛ ደረጃ ዕድገት አሳይቷል።

የትራንስፖርት ዘርፉን በቴክኖሎጂ ከመደገፍ አኳያ፤ የስምሪት ቁጥጥር፣ የትራፊክ ቅጣት ክፍያ፣ እንዲሁም 36 የሚሆኑ ዋና ዋና የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ አገልግሎቶች በዲጂታል ስርዓት እንዲሰጡ ተደርጓል። ይህም አሰራሩን ቀልጣፋ በማድረግ፣ ቅሬታን በመቀነስና የደንበኞችን እርካታ በማሳደግ ረገድ ጉልህ ለውጥ አምጥቷል።

የመኖሪያ ቤት አቅርቦትና አስተዳደር በተመለከተ፡-

የነዋሪውን የቤት ጥያቄ ለመመለስ ባለፉት አምስት ዓመታት 496,971 ቤቶች ተገንብተዋል። ከእነዚህም ውስጥ 26,563 የመንግስት ቤቶች ለልማት ተነሺዎች፣ እንዲሁም ከ98 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በእጣ ተላልፈዋል። በአሁኑ ወቅትም በተለያዩ አማራጮች የ179,516 ቤቶች ግንባታ በመፋጠን ላይ ነው።

በፋይናንስ አስተዳደር በኩል፤ ለረጅም ዓመታት የነበረ 62 ቢሊዮን ብር የጋራ መኖሪያ ቤት የባንክ ዕዳ የተከፈለ ሲሆን፣ በዘንድሮው በጀት ዓመትም 3.18 ቢሊዮን ብር የቦንድ ዕዳ ተመልሷል። 

በቤት አስተዳደር ዘርፍ ደግሞ የአከራይ ተከራይ ውል ምዝገባና ቁጥጥር የመጀመሪያ ምዕራፍ እየተጠናቀቀ የኪራይ ዋጋ ተመን ተወስኗል። በዚህም ከ500 ሺህ በላይ የነባር ውል እድሳትና አዳዲስ ምዝገባ ለማድረግ ዝግጅት ተጠናቋል።

ከኢንቨስትመንት በተመለከተ:-

በከተማችን የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለማስፋፋት በተደረገው ጥረት ባለፉት አምስት ዓመታት ለ22,190 ኢንቨስተሮች አዲስ፣ ለ1,632 ኢንቨስተሮች ደግሞ የማስፋፊያ ፍቃድ ተሰጥቷል። ከነዚህም ውስጥ ከ2 ሺህ በላይ የሚሆኑት ከ54 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል በማንቀሳቀስ ወደ ስራ በመግባት ሰፊ የስራ እድል ፈጥረዋል።

በተጨማሪም በመንግስትና የግል ዘርፍ አጋርነት (PPP) በተከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶች ከ1.3 ትሪሊዮን ብር በላይ ካፒታል መሳብ ተችሏል። ይህ አሰራር የግል ባለሀብቱን ተሳትፎ በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ የመንግስት በጀት ለሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች እንዲውል ከማስቻሉም በላይ፤ የከተማዋን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ከፍ የሚያደርጉ ልማቶችን እውን እያደረገ ይገኛል።

በግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር የእስታንዳርዳይዜሽን ስራዎች በተመለከተ

በመዲናዋ የሚገነቡ ግንባታዎች የከተማዋን ትልቅነት አህጉርና አለም አቀፍ ሚናን የማይመጥኑትን  በማጥናት መጠነ ሰፊ የእርምትና የስታንዳርዳይዜሽን ስራ ማከናወን ተችሏል፡፡ በዚህም ቡራቡሬ የነበረው የቀለም አይነት፣ የህንፃ ከፍታ፣ የመብራት የክላይዲንግና የእድሳት ችግሮችን በመለየት የማረምና የማስተካከል ስራዎች ተሰርተዋል፡፡

ለ138,731 የግንባታ ፈቃድ በመስጠት፣ ለ50,745 አዲስ የግልና የመንግስት ግንባታዎች የክትትልና የቁጥጥር ስራ በመፈጸምና አስፈላጊ የእርምት እርምጃዎችን በመውሰድ የግንባታ ጥራትን ማረጋገጥ ተችሏል።

በበጀት አመቱ በከተማዋ 68,002 ሕገ-ወጥ የሆኑ የውጭ ማስታወቂያዎችን በመለየትና ተገቢ የእርምት እርምጃ   ተወስዷል።በውጤቱም የከተማችን መለያ የሆኑ ቀለም፣ የህንፃዎች ክላዲንግ፣ ፋሳድና የወረቀት ማስታወቂያዎች ወደ ዲጂታል መቀየር ተችሏል፡፡

ስራ እድል ፈጠራ በተመለከተ

የከተማዋ አስተዳደር የስራ አጥነትን ለመቀነስ እና የስራ ባህልን ለማሳደግ በተሰራው ስራ ጉልህ ውጤቶች ተመዝግበዋል። ባለፉት አምስት ዓመታት ለ 2.2 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች የስራ እድል ተፈጥሯል።  ከእነዚህ ውስጥ 52% ሴቶች ሲሆኑ፣ 77% ደግሞ ወጣቶች ናቸው። 276,018 አንቀሳቃሾች በ53,840 (97%) ኢንተርፕራይዞች ተደራጅተው ወደ ስራ ገብተዋል።

በበጀት አመቱ በሥራ ፈላጊነት ለሆኑ 371,354 የሥራዕድል ለመፍጠር የተቻለበት ከእነዚህም 53% ሴቶች፣ 51.87% ወጣቶች እና 8.94% ምሩቃን ሲሆኑ 50% በኢንተርፕራይዝ በማደራጀት የተፈጠረ የሥራ ዕድል ነው።

በዘርፍ ስንመለከት በከተማ ግብርና ዘርፍ 35,779 (9.63%)፣ በኢንዱስትሪ ዘርፍ 97,692 (26.31%) እና በአገልግሎት ዘርፍ 23 ናቸዉ።

 የወንዝ ዳርቻ ልማት በተመለከተ፤-

በከተማዋ በ8 ወንዞች 59 ኪሎ ሚትር ርዝመት ያላቸዉ የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራዎች ተሰርቷል ፡፡

ይህም 6ሺ ሄክታር መሬት የሚሸፍን ሲሆን 16 የኮሪደር ልማት እና 2ሺህ ሄክታር የአረንጓዴ ልማት ሽፋን ያካተተ ነዉ፡፡

በተመሳሳይም 24 የውሃ ግድቦች፣ 66 ቼክዳሞች፣ 3 ሰው ሰራሽ ሀይቆች፣ 51 የእግረኛ ድልድዮችና መሰል መሰረተ ልማቶችን ያካተተው የወንዝ ዳርቻ ልማት የላቀ  ውጤት የተመዘገበበት ነዉ ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ሴቶችና ለችግር የተጋለጡ ዜጎች ተጠቃሚነት በተመለከተ!

በተማዋ በተፈጠረው ከ2 ሚሊዮን በላይ የሥራ ዕድል ውስጥ 52 በመቶ ለሴቶች የተሰጠ ሲሆን፣ በቤት አቅርቦትም 30 በመቶ ቅድሚያ ተሰጥቷቸው 147,080 ሴቶች የቤት ባለቤት ሆነዋል። በተጨማሪም 57,901 ሴቶች የብድር አገልግሎት አግኝተው 18.49 ቢሊዮን ብር መቆጠብ የቻሉ ሲሆን፣ የሥራ ቦታ፣ የማሽነሪ ሊዝና 5 ዘመናዊ የእንጀራ ፋብሪካዎችም ቀርበውላቸዋል።

ማህበራዊ አካታችነትን ባረጋገጠው በዚህ ስራ 5,887 አካል ጉዳተኞች ሰልጥነው ወደ ስራ የገቡ ሲሆን፣ 8,019 የሚሆኑት የሰው ሰራሽ አካልና ድጋፍ አግኝተዋል።

በሌላ በኩል 46,590 በጎዳና ላይ የነበሩ ዜጎች ተነስተው ወደ ስራ፣ ተሀድሶና ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደርጓል። አቅመ ደካሞችን ለመደገፍ በተዘረጉ 30 "የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላት" በቀን በአማካይ ለ35 ሺህ ሰዎች ምገባ እየቀረበ ሲሆን፣ ከእነዚሁ ተጠቃሚዎች መካከል ለ3 ሺህ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል በመፍጠር ከተማዋን ለሁሉም ነዋሪዎች እኩል ምቹ የማድረግ ታላቅ ስኬት ተመዝግቧል፡፡                        ከንቲባ አዳነች አቤቤ

 

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.