ከተማችንን የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግና የከተማ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ከተማችንን የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግና የከተማ ዲፕሎማሲ ስራዎች በተመለከተ

የጎብኚዎች ቁጥር መናር፡ የአገር ውስጥ ጎብኚዎች ቁጥር ከ4.1 ሚሊዮን ወደ 10.5 ሚሊዮን፤ የውጭ ቱሪስቶች ቁጥር ደግሞ ከ123,489 ወደ 1.2 ሚሊዮን አድጓል።

የገቢ ዕድገት፡ ከውጭ ቱሪዝም የሚገኘው ገቢ ከ5.63 ቢሊዮን ብር ወደ 242.6 ቢሊዮን ብር ያደገ ሲሆን፣ ከአገር ውስጥ ቱሪስቶች ደግሞ 63.3 ቢሊዮን ብር ወደ ከተማዋ ኢኮኖሚ ፈሷል።

የኮንፈረንስ ቱሪዝም፡ በበጀት ዓመቱ 221 ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ኮንፈረንሶች በስኬት ተስተናግደዋል፤ መዳረሻዎችንም እንዲጎበኙ ተደርጓል።

ከተማ ዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ትስስር፤ የእህትማማች ከተሞች ትስስር፡ ከተማዋ ከዓለም አቀፍ ከተሞች ጋር ያላት ትስስር ከነበረበት 20 ወደ 30 ከተሞች ከፍ ብሏል።

ሽልማቶችና እውቅናዎች (Smart City)

👉 የሴኡል ስማርት ከተማ ሽልማት (2024)
👉የአፍሪካ ምርጥ ስማርት ከተማ
👉ሽልማት (ናይሮቢ፣ 2024)
👉ለቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት የ“C40
👉ከተሞች የብሉምበርግ ሽልማት” (ቦነስ አይረስ)
 👉በሪዮ ዴጄኔሪዮ የተሰጠ የምገባ ፕሮግራም ሽልማት
 👉በመንገድ ደኅንነትና ፍጥነት ማስተዳደር ዘርፍ የዓለም አቀፍ ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ መሆን።
 ዓለም አቀፍ አባልነት፡ አዲስ አበባ የብሉምበርግ ፊላንትሮፒስ የከተሞች ጥምረት አባል ለመሆን በቅታለች።

 ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.