የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የ2018 ዓ.ም ሪፖርት እና የ2019 ዋና ዋና አቅጣጫዎችን ለከተማው ምክር ቤት እያቀረቡ ይገኛሉ።
7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ በተመለከተ:-
7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ የዲሞክራሲና የፖለቲካ ባህል መሻሻል የታየበት እና በርካታ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በምክር ቤት ወንበር የገኙበት ይህም ህዝባችንን በትብብር ለማገልገልና የጋራ ሀገራችንን ለመገንባት ወደ አዲስ ምዕራፍ የተሻገርንበት ከለዉጡ ማግስት ጀምሮ የተጎናፀፍነዉ የዚህ ትዉልድና ዘመን ድምር ዉጤታችን ነዉ፡፡
ተቋም ግንባታ በተመለከተ:-
አዳዲስ ሪፎርሞችና አሰራሮች፡- በየተቋሙ የተጀመሩ አዳዲስ የሪፎርም ስራዎችን በመተግበር "በወርቃማዋ ሰኞ" አመራርና ሰራተኛው ስለተልዕኮው የሚወያዩበት፣ በረቡዕ እና አርብ ደግሞ አመራሩ ተገልጋዮችን በአካል የሚያስተናግድበት አሰራር ሰፍኗል። በዚህም 87 በመቶ ተገልጋዮች በአግባቡ አገልግሎት ማግኘት ችለዋል። ከዚህም በተጨማሪ የተገልጋዮች መማክርት ጉባኤን በማቋቋም ተሳትፎን የሚያሳድግና ሌብነትን የሚቀንስ ሥርዓት ተዘርግቷል።
የተቋም ግንባታ እና አገልግሎት አሰጣጥ በተመለከተ
የከተማ አስተዳደሩ የተቋማት አገልግሎት እንዲዘምን በሰጠው ልዩ ትኩረት መሰረት ዋና መስሪያ ቤትን ጨምሮ 11 አዲስ "መሶብ" የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ተከፍተዉ ወደ ስራ በመግባታቸዉ 150 የሚሆኑ አገልግሎቶች በአንድ ማዕከል እየተሰጡ ይገኛሉ፡፡
ከዚህ ጎን ለጎን ከ8 ተቋማት የተለዩ 41 የሚደርሱ አገልግሎቶች በከተማው ውስጥ ህዝብ በሚበዛባቸው አደባባዮች በመገኝት ተንቀሳቃሽ የአዲስ መሶብ አገልግሎት እየተሰጠ ሲሆን በአዲስ መሶብ ማዕከላት እስካሁን 262,784 በላይ ለሚሆኑ ተገልጋዮች አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ በእነዚህ ማእከላት የተገለገሉ የተገልጋዮች እርካታ በአማካይ 99 በመቶ ደርሷል።
ወደ ማእከሉ ያልገቡ 45 አገልግሎቶች ዲጂታላይዝ በማድረግ አገልግሎት እየሰጡ በመሆኑ አጠቃላይ በዲጂታል የሚሰጡ አገልግሎቶችን ወደ 392 ማሳደግ ተችሏል፡፡
ሰላምና ፀጥታ በተመለከተ:-
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት ባለፉት አምስት ዓመታት በአዲስ አበባ የተለያዩ ሰላምን የማወክ ሙከራዎች ቢኖሩም፣ የጸጥታ መዋቅሩ ከህዝቡ ጋር በቅንጅት በሰራው ስራ አዲስ አበባ ፍጹም ሰላማዊ ሆና ቆይታለች ብለዋል። ከ200 ሺህ በላይ የሰላም ሰራዊት እና ከ10 ሺህ በላይ የህዝብ ጥበቃዎችን በማደራጀት ነዋሪው የሰላሙ ባለቤት እንዲሆን በማድረግ ከተማዋን "የሰላም ከተማ" ማስባል ተችሏል።
•የህግ የበላይነትና ወንጀል መከላከል፡- እንደ ህገ-ወጥ መሬት ወረራ፣ ህገ-ወጥ ግንባታ እና የጎዳና ንግድ ያሉ የደንብ ጥሰቶችን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ የተቻለ ሲሆን፤ የተጠናከረ የቁጥጥር ስራ በመሰራቱ ከባድ ወንጀሎች ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀሩ ከ47 በመቶ በላይ ቀንሰዋል።
ሌብነትና ብልሹ አሰራርን ከማስቀረት አንፃር የተሰሩ ስራዎች
ሌብነትንና ብልሹ አሰራርን በተጨባጭ ለመታገል በተያዘው ቁርጠኝነትና በጥፋት ላይ ተሰማርተው በተገኙ በአጠቃላይ 5,857 አካላት ላይ ( 79 ሹመኛ አመራሮች፣ 213 የሜሪት አመራሮች፣ 5,430 ባለሙያዎች እና 135 ተገልጋዮች ) እንደ ጥፋታቸው ክብደት ከማስጠንቀቂያ እስከ ስንብትና በህግ ተጠያቂ ማድረግ የሚደርሱ እርምጃዎች ተወስደዋል።
የረቡዕና አርብ የባለጉዳይ ቀናት ላይ በተደረገ ምልከታ በአማካይ 90% አመራርና፣ ሰራተኞች በስራ ገበታ በመገኘት አገልግሎት እየሰጡ ነው። በዚህም በበጀት አመቱ አገልግሎት ከጠየቁ ተገልጋዮች ከ87% በላይ አገልግሎት ማግኘት ችለዋል፤
አገልግሎትን ግልፅና ተጠያቂነት የሰፈነበት ለማድረግ በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ “ አገልጋዩ ” የሚል አመራሩ ከሕዝብ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጥበት የቀጥታ ስርጭትና “ ዋርካ ” የሚል አገልጋዩና ሕዝቡ በአካል ተገናኝቶ ፊት ለፊት የሚጠያየቅበት ኘሮግራም ተግባራዊ በማድረግ 89 % የሚሆኑት ችግሮች መፍታት ተችሏል።
የመንግስት ሰራተኞችን የኑሮ ጫና ከግንዛቤ ያስገባ ሁለት ጊዜ የደሞዝ ጭማሪ የተደረገ ሲሆን፣ በተጨማሪም በቢሊዮን በጀት በመመደብ የሰራተኞች ካፍቴሪያ ድጐማ፣ በየተቋማት የሸማቾች ሱቅና የህፃናት ማቆያዎችን ከነሙሉ ወጪው አደራጅተን አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡
ከመማር ማስተማር አንፃር፡-
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለከተማው ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት፤ የከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት የተማሪዎችን ተደራሽነት፣ አካታችነትና የትምህርት ጥራት በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ መቻሉን አስረድተዋል። በዘርፉ የተመዘገቡ ዋና ዋና ስኬቶች ፡-
•የተደራሽነት ዕድገት፡- ባለፉት አምስት ዓመታት የተማሪዎች ቁጥር ከ829,158 ወደ 1,334,830 ከፍ ብሏል። በ2018 በጀት ዓመትም ይህንኑ የተማሪዎች ቁጥር በማሳካት ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ81,093 ብልጫ ማሳየት ተችሏል።
•የትምህርት ጥራትና ውጤት፡- ጥራትን ለማረጋገጥ በተሰራው ስራ የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና አላፊዎች ከ80.2% ወደ 97%፣ የ8ኛ ክፍል ከ36.1% ወደ 96.2%፣ እንዲሁም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና አላፊዎች ከ25.45% ወደ 31% ማደጉን አብራርተዋል።
•የትምህርት ግብዓት አቅርቦት፡- የመፅሐፍና ተማሪ ጥምርታን 1፡1 ማድረስ የተቻለ ሲሆን፤ የደብተርና ዩኒፎርም አቅርቦትም ትምህርት ከመጀመሩ አስቀድሞ በክረምቱ ሙሉ በሙሉ ለተማሪዎች ተደራሽ ሆኗል።
•አካታች ትምህርት፡- የልዩ ፍላጎት ትምህርትን በማስፋፋት 124 ማዕከላት ተደራጅተው 34,117 ተማሪዎች የትምህርት ዕድል አግኝተዋል። ለአይነ ስውራንና ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች የብሬል መፃህፍት፣ የድምጽ መሳሪያዎች እና የተለያዩ የአካል ድጋፍ ግብዓቶች ቀርበውላቸዋል።
•የትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ፡- ማህበረሰቡን በማስተባበር 13 ቢሊዮን ብር የሚገመት ሀብት (በገንዘብ፣ በአይነት፣ በጉልበትና በእውቀት) በማሰባሰብ የትምህርት ቤቶችን የመጠገንና ግብዓት የማሟላት ስራ መሰራቱን ከንቲባዋ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የተማሪ ምገባን በተመለከተ:-
ከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ በጀት በመመደብ የተማሪ ምገባ ፕሮግራም ወደ 1 ሚሊዮን ለሆኑ ተማሪዎች በቀን ሁለት ጊዜ ጥራት ባለው መልኩ ተደራሽ ማድረግ ተችሏል።
በምገባ ፕሮግራሙ ከ 2ዐ ሺህ በላይ ለሆኑ እናቶች የስራ እድል መፍጠር የተቻለ ሲሆን በኢኮኖሚያዊ ጫና ምክንያት ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ፣ የሚደግሙ እና የሚያረፍዱ ተማሪዎች ጉልህ በሆነ መልኩ መቀነስ አስችሏል። በዚህም በተማሪዎች የትምህርት ውጤት እና አካላዊ ጤናማ እድገት ላይ ጉልህ መሻሻሎች ተመዝግበዋል፡፡
ከመማር ማስተማር አንፃር፡-
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለከተማው ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት፤ የከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት የተማሪዎችን ተደራሽነት፣ አካታችነትና የትምህርት ጥራት በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ መቻሉን አስረድተዋል። በዘርፉ የተመዘገቡ ዋና ዋና ስኬቶች ፡-
•የተደራሽነት ዕድገት፡- ባለፉት አምስት ዓመታት የተማሪዎች ቁጥር ከ829,158 ወደ 1,334,830 ከፍ ብሏል። በ2018 በጀት ዓመትም ይህንኑ የተማሪዎች ቁጥር በማሳካት ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ81,093 ብልጫ ማሳየት ተችሏል።
•የትምህርት ጥራትና ውጤት፡- ጥራትን ለማረጋገጥ በተሰራው ስራ የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና አላፊዎች ከ80.2% ወደ 97%፣ የ8ኛ ክፍል ከ36.1% ወደ 96.2%፣ እንዲሁም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና አላፊዎች ከ25.45% ወደ 31% ማደጉን አብራርተዋል።
•የትምህርት ግብዓት አቅርቦት፡- የመፅሐፍና ተማሪ ጥምርታን 1፡1 ማድረስ የተቻለ ሲሆን፤ የደብተርና ዩኒፎርም አቅርቦትም ትምህርት ከመጀመሩ አስቀድሞ በክረምቱ ሙሉ በሙሉ ለተማሪዎች ተደራሽ ሆኗል።
•አካታች ትምህርት፡- የልዩ ፍላጎት ትምህርትን በማስፋፋት 124 ማዕከላት ተደራጅተው 34,117 ተማሪዎች የትምህርት ዕድል አግኝተዋል። ለአይነ ስውራንና ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች የብሬል መፃህፍት፣ የድምጽ መሳሪያዎች እና የተለያዩ የአካል ድጋፍ ግብዓቶች ቀርበውላቸዋል።
•የትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ፡- ማህበረሰቡን በማስተባበር 13 ቢሊዮን ብር የሚገመት ሀብት (በገንዘብ፣ በአይነት፣ በጉልበትና በእውቀት) በማሰባሰብ የትምህርት ቤቶችን የመጠገንና ግብዓት የማሟላት ስራ መሰራቱን ከንቲባዋ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ሥራዎችን በተመለከተ
የትምህርትና ስልጠና ተቋማት ህጋዊነታቸውን ከማረጋገጥ አኳያ ለ184 አዲስ የእውቅና ፍቃድ የተሰጠ ሲሆን፣ በትምህርት አገልግሎት ክፍያ ደንብ ቁጥር በሚመለከት በ1‚227 ትምህርት ቤቶች ክትትልና ቁጥጥር በማድረግና በ1‚916 ተቋማት የድንገተኛ ኢንስፔክሽን የተደረገ ሲሆን በስርዓተ ትምህርትና ስልጠና ላይ ጥሰት ፈፅመው በተገኙ 372 የትምህርት ተቋማት ላይ የእርምት እርምጃ ተወስዷል።
አረንጓዴ አሻራ በተመለከተ:-
በአረንጓዴ አሻራ የልማት ስራ፣ ቀደም ሲል 2.8 በመቶ ብቻ የነበረውን የከተማዋን የአረንጓዴ ሽፋን ባለፉት አምስት ዓመታት ወደ 24 በመቶ ማሳደግ ተችሏል። ከተማዋን ውብና ማራኪ ለማድረግ 7 ሺህ ሄክታር መሬት ለአረንጓዴ ልማት የዋለ ሲሆን፤ የችግኝ ተከላና እንክብካቤ ስራዎችም በስፋት ተከናውነዋል። በተጨማሪም እነዚህን አረንጓዴ ስፍራዎች ከህገ-ወጥ ወረራ ለመጠበቅ ለ266 ቦታዎች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ተዘጋጅቶላቸዋል።
ከጤና አገልግሎት በተመለከተ:-
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፉት አምስት ዓመታት ከተማዋን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ በሰራው ስራ፤ የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት ከእጥፍ በላይ በማደጉ የእናቶችና የጨቅላ ህፃናት ሞት ምጣኔን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ መቻሉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሪፖርታቸው ገልጸዋል።
በመሰረተ ልማት ረገድ፤ አዳዲስ እና ግዙፍ ሆስፒታሎች (እንደ አበበች ጎበና፣ ላፍቶ፣ ኮልፌ እና ገላን) እንዲሁም 9 አዳዲስ ጤና ጣቢያዎች ተገንብተዋል። የሆስፒታል አልጋዎች አቅም ከ1,384 ወደ 4,195 ያደገ ሲሆን (ይህም ባለፉት 100 ዓመታት ከተመዘገበው በእጥፍ ይበልጣል)፣ የአምቡላንስ ቁጥርም ወደ 109 ከፍ ብሏል። ሆስፒታሎቹም በዘመናዊ መሣሪያዎች ማለትም በMRI እና ሲቲ ስካን ተደራጅተዋል።
በማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን 2.7 ሚሊዮን ነዋሪዎች የታቀፉ ሲሆን፤ ከተማ አስተዳደሩ በየዓመቱ ከ1.3 ቢሊዮን ብር በላይ ድጎማ ያደርጋል። የወረቀት አልባ የጤና መረጃ ስርዓትም (EMR) በ68 ተቋማት ተተግብሯል። በተጨማሪም ለማህበራዊ ፍትህ ሲባል ለ200 ታካሚዎች በዓመት 100 ሚሊዮን ብር በመመደብ ነፃ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል።
በሌላ በኩል የህዝብን ጤና ለመጠበቅ በተደረገ ጥብቅ ቁጥጥር፤ 193 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው 350 ሺህ ኪሎ ግራም የምግብ ምርቶች፣ 42 ሺህ ሊትር መጠጦች፣ እና 21 ሺህ ኪሎ ግራም ጊዜ ያለፈባቸው መድሃኒቶች እንዲወገዱ መደረጉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለምክር ቤቱ አብራርተዋል።
ፅዳት በተመለከተ
በደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ከ5 ሚሊዮን ቶን በላይ ቆሻሻ ተሰብስቧል። የቆሻሻ አያያዝን ከመጣል ባለፈ ወደ 484 ሺህ ቶን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል፣ ኮምፖስት በማምረት እና ከ910 ሺህ ቶን በላይ ለኃይል ማመንጫ በማቅረብ ቆሻሻን ወደ ሀብትነት መቀየር ተችሏል። በዚህም አዲስ አበባ ከአፍሪካ 10 ፅዱ ከተሞች አንዷ በመሆን ዓለም አቀፍ እውቅናን አግኝታለች።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.