አዲስ አበባ ከአፍሪካ አስር ፅዱ ከተሞች አንዷ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አዲስ አበባ ከአፍሪካ አስር ፅዱ ከተሞች አንዷ ሆናለች!! የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የ2018 ዓ.ም ሪፖርት እና የ2019 ዋና ዋና አቅጣጫዎችን ለከተማው ምክር ቤት እያቀረቡ ይገኛሉ።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ  አዳነች አቤቤ የ2018 ዓ.ም ሪፖርት እና የ2019 ዋና ዋና አቅጣጫዎችን ለከተማው ምክር ቤት እያቀረቡ ይገኛሉ።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ እያቀረቡ ባለው ሪፖርት፤ ባለፉት አምስት ዓመታት ከተማዋን የሰላምና የልማት ማዕከል ለማድረግ ስር ነቀል ለውጦች መደረጋቸውንና እንደ አድዋ ድል መታሰቢያ ያሉ የወል ትርክት መሰረቶች መገንባታቸውን ገልፀዋል።

የከተማዋ ጎስቋላነት ከ74% ወደ 30% መቀነሱን፣ የ2.8% አረንጓዴ ሽፋን ወደ 24% ማደጉን እና መዲናዋ ከአፍሪካ አስር ፅዱ ከተሞች አንዷ መሆኗን ገልጸዋል። የጎዳናዎች መስፋትና መብራት የአዲስ አበባን የኮንፈረንስና ዲፕሎማሲ ማዕከልነት ይበልጥ እንዳጎላው አብራርተዋል።

በማህበራዊ ፍትህ፤ የተማሪዎች ምገባ፣ የቤት ግንባታ፣ የሥራ ዕድል ፈጠራና የኑሮ ውድነትን የማቃለል ሥራዎች በስፋት መከናወናቸውን አንስተዋል። መዲናዋ በራስ ገቢ ከ60 ሺህ በላይ ፕሮጀክቶችን እንዳጠናቀቀችም ገልጸዋል።

በተጨማሪም ብክነትንና ሌብነትን በማስቀረት ለዘላቂ ልማት የሚመደበውን የበጀት መጠን ከ47% ወደ 71% ማሳደግ መቻሉ የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጡን ከንቲባዋ ለምክር ቤቱ እያቀረቡ ባለው ሪፖርት አብራርተዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.