የጎንዮሽ ህገወጥ የቤት ኪራይ ውል የአከራይ ተከ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የጎንዮሽ ህገወጥ የቤት ኪራይ ውል የአከራይ ተከራይ አዋጅን የሚፃረርና በህግ የሚያስጠይቅ ነው

የጎንዮሽ ህገወጥ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል የወጣውን የአከራይ ተከራይ አዋጅ የሚፃረር መሆኑንና በህግም እንደሚያስጠይቅ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቅድስት ወልደ ጊዮርጊስ አሳሰቡ።

‎ቢሮው በከተማዋ ካሉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ማህበራት ተወካዮች ጋር ውይይት አድርጓል።

‎"የአከራይ ተከራይ ግንኙነትን በህግ ማዕቀፍ በመምራት የጋራ ተጠቃሚነትን እናረጋግጣለን" በሚል መሪ ሀሳብ በተደረገው ውይይት ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ከ1 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤት ማህበራት ተወካዮች ተገኝተዋል።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቅድስት ወ/ጊዮርጊስ በህገወጥ ደላሎች አነሳሽነት የጎንዮሽ ህገወጥ ውሎች እየተፈፀሙ እንደሚገኙ ከመንግስት ድብቅ እንዳልሆነ ጠቅሰዋል።

ይህ ድርጊት ግን የታሰበውን የጋራ ተጠቃሚነት እንደማያረጋግጥና በህግም እንደሚያስጠይቅ አስጠንቅቀዋል።

‎በቅርቡ የአከራይ ተከራይ አዋጅን መነሻ በማድረግ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ጣራው 11.5 በመቶ የሆነ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ማሻሻያን ማፅደቁ ይታወሳል።

‎ANN


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.