"የአፍሪካ የህክምና ትምህርት ጉባኤ" ተሳታፊዎች...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"የአፍሪካ የህክምና ትምህርት ጉባኤ" ተሳታፊዎች በመዲናዋ የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎችንና ታሪካዊ ቦታዎች ጎበኙ።

ከ52 በላይ ሀገራትን ያሳተፈው "2ኛው የአፍሪካ የህክምና ትምህርት አህጉራዊ ጉባኤ" በአዲስ አበባ ተካሂዷል:: የጉባኤው ተሳታፊዎች በቆይታቸው፣ በአዲስ አበባ የሚገኙ  የቱሪዝም መዳረሻዎችንና ታሪካዊ ስፍራዎችን ጎብኝተዋል::

ከቅርብ አመታት ወዲህ በርካታ አለም ዓቀፍ እና አህጉር ዓቀፍ ጉባኤዎችን በብቃት እያስተናገደች የምትገኘው አዲስ አበባ፣ በኮንፍረንስ ቱሪዝም እድገት መሠረታዊ ለውጥ እያስመዘገበች ትገኛለች::

የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን፣ የተለያዩ ጉባኤ ተሳታፊዎች ከሚያካሂዱት ጉባኤ ጎን ለጎን፣ በመዲናዋ የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎችን እንዲጎበኙ በርካታ የማስተዋወቅ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል::


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.