በድል የተጠናቀቀውን የ2018 ዓ.ም ጠቅላላ ምር...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በድል የተጠናቀቀውን የ2018 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫ በሚመለከት፦

‎የዘንድሮ ምርጫ ለየትኛውም የፖለቲካ አካል እጅግ አስተማሪና የኢትዮጵያን ህዝብ ጥልቅ አሳቢነትና ሰላም ወዳድነት በትልቁ ያሳየ ትልቅ ታሪካዊ ሁነት ሆኖ ተመዝግቧል። የዘንድሮ ምርጫ ከሌላው ጊዜ በተለየ ከፍተኛ ተግዳሮት ገጥሞት ነበር፤ ከዚህ በፊት እንደተለመደው ፍጥጫው በተፎካካሪዎች መሀል ብቻ አልነበረም፤ ይልቁንም እራሱ ምርጫው የተጠናከረ ጥቃት ኢላማ ነበር። ነገር ግን ማሸነፍና ፈተና መሻገር እንዲሁም ሀገር በማጽናት ልምዳቸው የሚታወቁት ኢትዮጵያውያን ምርጫውን በማካሄድ ጽንፈኝነትን እና ዘረኝነትን አሻፈረኝ በማለት ከዳር እስከዳር ድምጹን አስተጋብተዋል። በተጨማሪም በአፍሪካና በዓለም የዲሞክራሲ ታሪክ መኖሩን በሚያጠራጥር ሁኔታ ብልጽግና ፓርቲ በ85 በመቶ መቀመጫ በመወዳደርና የተቀረውን ለተፎካካሪ ፓርቲዎች በመተው፤ ታላቅ የዲሞክራሲ ቀናዒነት የታየበት ምርጫ ነበር።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.