በ6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተነሡ ጥያቄዎች፦
የወደብ የኅልውናችን ጉዳይ ነው፤ የወደብና የባህር በር ጉዳይ ምን ደረጃ ላይ እንዳለ ቢገልጹልን?
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሂደት በተያዘለት የጊዜ ሠሌዳ መሠረት ተጠናቅቆ የታለመለትን ሀገራዊ ዓላማ እንዲያሳካ መንግሥት በቀጣይ ምን ዓይነት የሎጂስቲክስ፣ ፖለቲካዊና ተቋማዊ ድጋፍ ያደርጋል?
ተጀምረው ላልተጠናቀቁ እና ታቅደው ላልተጀመሩ ፕሮጀክቶች ምን የታሰበ ነገር አለ?
አነስተኛ ገቢ ላላቸው እና ለመንግሥት ሠራተኞች የኑሮ ጫናን ለመቋቋም ምን ታስቧል፤ ከሚመሠረተው አዲሱ መንግሥት ምን እንጠብቅ?
የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ስለሆነ ለሁሉም ክልሎች አስገዳጅ ሆኖ ቢቀርብ?
የመንግሥት መዋቅር ተጠቅሞ በዜጎች ላይ ምዝበራ የሚፈጽሙ አካላት ላይ ገዥው ፓርቲ መዋቅሩን የማጽዳት እና ተጠያቂነትን የማስፈኑን ጉዳይ እንዴት ሊያስተካክለው አስቧል?
ከፀጥታ አኳያ እየተሻሻሉ ያሉ ጉዳይ ቢኖርም፣ አሁንም አንዳንድ ቦታዎች ችግሮች አሉ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን መፍትሔ ለመስጠት ታስቧል?
ከነዳጅ ጋር በተያያዘ፦ መንግሥት ለነዳጅ ድጎማ ቢያደርግም የነዳጅ ሽያጭ እና ስርጭት ከብልሹ አሠራር ሊድን አልቻለም። በዚህ ላይ መንግሥት የያዘው መፍትሔ ምንድን ነው?
በትግራይ ክልል ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ እና የትግራይ ሕዝብ የሰላም እንዲያገኝ በመንግሥት በኩል እየተደረገ ያለውን ጥረት ቢያሳውቁን?
ሰላምን ወደ ዘላቂ መሠረት ለማሸጋገር ከምሁራን፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከህዝቡ ምን አይነት ንቁ ተሳትፎ ይጠበቃል?
በትላልቅ ፕሮጀክቶች ምክንያት የሚነሡ ዜጎች መብት በአግባቡ እየተጠበቀ አይደለም የሚል ቅሬታ አለ። ፍትሐዊ የሆነ የካሳ አከፋፈል እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ምን ይደረጋል?
የጠቅላይ ኦዲተር ሪፖርቶች ተደጋጋሚ የፋይናንስ ጉድለቶችን ቢያሳዩም፣ ተጠያቂነትን በማስፈን ረገድ ክፍተቶች አሉ። መንግሥት ተቋማትን ከሙስና እና ከመዝባሪ ኃይሎች ለማጽዳት ምን አዲስ አሠራር ይዘረጋል?
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.