ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ዘመናዊ የፖሊስ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ዘመናዊ የፖሊስ የመኖሪያ መንደር ግንባታን አስጀምረናል።

በከተማ አስተዳደራችን በፖሊስ ተቋም እየሰራናቸው ባሉ የሪፎርም ስራዎች እና ሰራዊቱ በህዝብ የተጣለበትን አደራ በአግባቡ እንዲወጣ የማድረግ ተግባር፣  “የሰራዊቱን መንደር እንገነባለን” ብለን የገባነውን ቃል  ዛሬ ወደ ተግባር አሸጋግረነዋል።
 
እያደገችና እየዘመነች ከመጣችው  የአፍሪካ እና 3ኛዋ የዓለም የዲፕሎማሲ ማዕከል የሆነችው መዲናችን አዲስ አበባን ለሚያገለግል የፖሊስ ሰራዊት  የጀመርነው የመኖሪያ ቤት ግንባታ ባለ 15 ፎቅ  የሆኑ 12 ህንፃዎች ሲሆኑ፤ የሰራዊቱ   አባላትን  ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች በመቀነስ በትጋትና በአግባቡ ህዝቡን እንዲያገለግል ለማድረግ ነው።
 
በኮሚሽኑ በከፍተኛ ትጋት የተጀመሩ  የሰራዊቱን አባላት በቴክኒክ፣ በእውቀት እና በቴክኖሎጂ ማስታጠቅ የሚያስችሉ ሥራዎች እንዲሁም የሰራዊቱን ህይወት ለማሻሻል  የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ድጋፋችንን  እጠናክረን እንቀጥላለን።
 
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.