ዛሬ የምስጋና ቀን ነው!!!ከንቲባ አዳነች አቤቤ

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ የምስጋና ቀን ነው!!!ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ዛሬ የምስጋና ቀን ነው!!!

አስጀምሮ ያስጨረሰን ፈጣሪ አምላክ የተመሰገነ ይሁን!
የእንጦጦ - ቀበና የወንዝና የወንዝ ዳርቻ ልማት በስኬት እንዲህ ባማረ መልኩ ለማጠናቀቅ፤ ለመጪው ትውልድ የሚተላለፍ ደማቅ አሻራ እንድናኖር አብራችሁን የሰራችሁ  የመሰረተ ልማት ተቋሞቻችን አመራሮች፣ ሰራተኞች፣ ኮንትራክተሮች፥ አማካሪዎች፣ የቀን ሰራተኞች፣ ባለሙያዎች፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ታላቅ አክብሮትና ምስጋናችን ይድረሳችሁ።

ያለማቋረጥ እንደዚህ ያሉ አዳዲስ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ሰርተን ለትውልድ ስጦታ አድርገን ስናቀርብ  በከተማችን በጀት እንጂ  በብድር ወይም  በእርዳታ አይደለም። በመሆኑም የከተማችን ግብር ከፋዮች፣ የገቢ ሰብሳቢና የፋይናንስ ተቋሞቻችን አንድ ላይ ተደምረን በትብብር ያሳካነው ልማት  በመሆኑ ሁላችሁንም በከተማችን ነዋሪዎች፣ በአስተዳደራችን እና በራሴ ስም ከልብ አመሰግናለሁ።
 
የከተማችን ነዋሪዎችን እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ፣ ይህንን እጅግ ውብና ማራኪ  የመዝናኛና ጤና መጠበቂያ ሆኖ የተጠናቀቀ የቀበና  ወንዝ እና የወንዝ ዳርቻ ልማት   በዋናነት የተሰራው ለእናንተ ነውና  መጥታችሁ እንድትጎበኙ፣ እንድትዝናኑ  እጋብዛችኋለሁ።
ልማቱንም በዘላቂነት ለትውልድ እንዲተላለፍ እንድትንከባከቡት እና  እየጠበቃችሁ  እድትጠቀሙበት እደራ እላለሁ። 
  
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.