ያስቀመጥናቸውን የምርጫ መንትያ ግቦች ያሳካው ህ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ያስቀመጥናቸውን የምርጫ መንትያ ግቦች ያሳካው ህዝባችን ነው! በ7ኛው ዙር ሃገራዊ ምርጫ ያሸነፈችው ኢትዮጵያ ናት ፤ ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ ያደረጉት ደግሞ ህዝቦቿ ናቸው።

ውድ የከተማችን ነዋሪዎች ምርጫውን ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊ፣ ነፃ ሆኖ በስኬትና በውጤት እንድናጠናቅቅ ስላደረጋችሁ እና የብልፅግና ፖሊሲና ስትራቴጂ ብሔራዊ ጥቅሞቻችን ያረጋግጣል ብላችሁ ፓርቲያችንን ብልፅግናን በአብላጫ ድምፅ ስለመረጣችሁ እናመሰግናለን። 

ሃገርን ማፅናት፣ ሰላምን ዘላቂ ማድረግ፣ ብሔራዊ ጥቅማችንን ማረጋገጥ የኢትዮጵያችን  የመቻል ማሳያዎች ናቸው ።
ለበርካታ የሚዲያ ዘመቻዎች፣ ከውጭም ከውስጥም ለነበሩ ጫናዎች ጆሮ ሳትሰጡ  የኢትዮጵያን የመቻል አቅም ያረጋገጣችሁ  የከተማችን ነዋሪዎችን  በፓርቲያችንና በመንግስታችን ሥም እናመሰግናለን።
 
ሌሊት ወጥታችሁ ከቴክኖሎጂ መስተጓጎል ጋር በተፈጠረው እንግልት ሳትሰላቹ፣ ቀኑን ሙሉ ደከመኝ ሳትሉ እስከሌሊት በፅናት በመሰለፍ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ እንዲረጋገጥ አድርጋችኋል። ልማታችን እንዲቀጥል፣ ሰላማችን እንዲረጋገጥ አድርጋችኋል። ፓርቲያችን ብልፅግናን  ስትመርጡ ምንም ችግር የለም ብላችሁ ሳይሆን፣ ያልተመለሱ ጥያቄዎች በሂደት ይመለሳሉ፣ ያልጨረስናቸው ስራዎች በሂደት ያልቃሉ፣ የጎደለው ይሞላል ብላችሁ እምነት ሰጥታችሁ ነው።
 የሰጣችሁን አደራ ነውና እኛም በታማኝነትና በመሰጠት፣ በትጋትና በቁርጠኝነት፣  24/7 በመስራት አዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ በቁርጠኝነት የምንሰራ መሆኑን ላረጋግጥላችሁ እፈልጋለሁ።
 
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.