የእንጦጦ - ቀበና የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክት

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የእንጦጦ - ቀበና የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክት

የእንጦጦ - ቀበና የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክት በጥቂቱ፦
‎
‎ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በይፋ የተመረቀው ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት ከያዛቸው መሰረተ ልማቶች ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፤
‎
‎- የወንዝ ልማት፦ 1 ትልቅ ግድብ፣ 16 አነስተኛ ግድቦች፣ 3 ቼክ ዳሞች እና 20.2 ኪ.ሜ የድጋፍ ግንብ።
‎
‎- የወንዝ ዳርቻ ልማት፦ 36,928 ካ.ሜ የአፈር እና ስነ-ምህዳር ጥበቃ ስራዎች (የኮንሶ ጋቢዮን እና እርከን)።
‎
‎- አረንጓዴ ልማት፦ 59.7 ሄክታር የአረንጓዴ ሽፋን እና 50,330 የተተከሉ ዛፎች።
‎
‎- የተቀናጀ መሰረተ ልማት፦ 21 የእግረኛ ድልድዮች፣ 33.2 ኪ.ሜ የውስጥ መንገዶች፣ የፍሳሽ መስመር እና 695 ተሽከርካሪዎችን ማቆም የሚያስችሉ 7 ቦታዎች።
‎
‎ይህ ፕሮጀክት ስነ-ምህዳሩን ከመቀየር ባለፈ፣ በውስጡ በያዛቸው ሱቆች፣ ካፌዎች እና የቱሪዝም መዳረሻዎች አዳዲስ የንግድና የኢኮኖሚ እድሎችን በመፍጠር የዜጎችን ተጠቃሚነት ያረጋግጣል።

#PMOEthiopia #EthiopiaDelivers


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.