“ወደፊት ለሚደረጉ የተለያዩ ንግድ ትርኢቶች አዲ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

“ወደፊት ለሚደረጉ የተለያዩ ንግድ ትርኢቶች አዲስ አበባ ቀዳሚ ምርጫችን ናት”

የዓለም አቀፍ ንግድ ትርኢት ተሳታፊዎች

በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው 8ኛው ዓለም አቀፍ "አግሮ ፉድ እና ፕላስትፕሪንትፓክ ኢትዮጵያ" እንዲሁም በ2ኛው "የኢትዮጵያ የምግብ እና የቡና ንግድ ትርኢት" ላይ ለመሳተፍ ከመላው ዓለም የመጡ ባለሀብቶች የኢንዱስትሪ መሪዎችና የዘርፉ ተዋናዮች በመዲናዋ የሚገኙ ታዋቂ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ጎበኙ።

ጉብኝታቸውን ያደረጉት እንግዶች በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙትን የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች፣ የወንዝ ዳር ልማት ስራዎችን እንዲሁም የከተማዋን ውብ የቱሪዝም መዳረሻዎች ተመልክተዋል።

በጉብኝታቸው ወቅት ተሳታፊዎቹ በከተማዋ በአጭር ጊዜ ውስጥ በተከናወኑ የልማት ስራዎች መደነቃቸውን ገልጸዋል። 

በተለይም አዲስ አበባ ለኮንፍረንስ ቱሪዝም ያላትን ምቹ መሠረተ ልማት እና ዘመናዊ ገጽታ ያደነቁት እንግዶቹ፣ ከተማዋ ለወደፊት የሚያዘጋጇቸው የንግድ ትርኢቶች ቀዳሚ ምርጫቸው እንደምትሆን ማረጋገጣቸውን የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን መረጃ ያመለክታል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.