ያቀድነው የምርጫ ግቦች ተሳክተው ለመመሰጋገን ያ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ያቀድነው የምርጫ ግቦች ተሳክተው ለመመሰጋገን ያበቃን ፈጠሪ የተመሰገነ ይሁን !

ውድ የከተማችን ባለሀብቶች ፓርቲያችን ብልፅግና ሃገራችንን ለመገንባትና ሁሉንም ኢትዮዽያዊ  ተጠቃሚ የሚያደርግ ፓሊሲና ስትራቴጂ ነድፎ እየተጋ መሆኑን ገብቷችሁ  ግልፅ አቋም ይዛችሁ የሁሌም አጋርነታችሁንና ግንባር ቀደም ሆናችሁ  በሁሉም መልኩ  በንቃት በመሣተፍ ላደረጋችሁት ድጋፍ ሁሉ በድጋሚ እናመሰግናለን።

የኢትዮጵያ ምርጫ የአንድ ፓርቲ አብላጫ ድምፅ ከማግኘት በላይ ከፍ ያለ ሀገርን የማፅናት ተግባር ነው ። ለዚህ ህዝባችን ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ያሳየውን ፅናት፥ የተጀመረው የሀገር ልማት ለማስቀጠል ያለውን ፍላጐት እና ሰላምን ዘላቂ የማድረግ  ጉዞ እንዲሳካ ለፓርቲያችን ዳግም ታላቅ ኃላፊነትና አደራ ሰጥቷል። በተሰጠን ሃላፊነት በእውነት፥ በትጋት እና በቅንነት በማገልገል ህዝባችንን እንክሳለን።

ፓርቲያችን በግሉ ሴክተር ጠንካራ  አጋርነት ብልፅግናችን ይሳካል ብሎ ያምናል። ለዚህም የግሉ ሴክተር ለሃገር ግንባታ በምታደርጉት ጥረት ሁሌም ድጋፋችን አይለያችሁምና በትብብር መስራታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.