በከተማ አስተዳደሩ ዓመታዊ የመኖሪያ ቤት ኪራይ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በከተማ አስተዳደሩ ዓመታዊ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ መወሰኛ ጥናት ላይ የፖናል ውይይት ተካሄደ

በእዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤናማ የቤት ኪራይ አሰራሮችን ለመዘርጋትና በህግ ማዕቀፍ ለመምራት የሚያስችል የግል መኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ መተመኛ ጥናትን አስመልክቶ የፓናል ውይይት ተካሄዷል። 

የቀረበው ጥናት በከተማዋ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ፋይዳዎች እንዳሉት በመድረኩ ላይ ተገልጿል። 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች  ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ቅድስት ወ/ጊዮርጊስ እንደገለጹት፡- ጥናቱ አከራዩ ወቅቱን ያገናዘበ ፍትሃዊ ገቢ እንዲያገኝ የሚያረጋግጥ  ተከራዩ ደግሞ ከገቢው ጋር የተመጣጠነ ኪራይ እንዲከፍል ለማስቻል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የዋጋ ትመና ጥናቱ በዘፈቀደ የተሰራ ሳይሆን የከተማችንን ነዋሪ የሆኑ ተከራዮች የመክፈል አቅም ያገናዘበ ነው ሲሉ የቢሮው ኃላፊዋ ገልጸዋል።

ይህ የኪራይ ዋጋ ማስተካከያ ጥናት በከተማችን  የኑሮ ውድነትን በመቀነስ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ  ፋይዳው የጎላ መሆኑንም የቢሮው ኃላፊ ቅድስት ወ/ጊዮርጊስ ገልጸዋል ።

መድረኩ ለ2019 በጀት ዓመት የተዘጋጀው የገበያ ዋጋ ጥናት ወደ ተግባር ከመሸጋገሩ በፊት ፣ ከሚመለከታቸው ተቌማት እና ከህዝብ ተወካዮች የጋራ ለማድረግ መሆኑ ተገልጿል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.