"ትክክለኛና ጥራት ያለዉ መረጃን በወቅቱ ለህብረተሰቡ ማድረስ የተቋማችን ኃላፊነት ነው" አቶ ኃፍታይ ገብረእግዚአብሔር
በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የተገነባው ዘመናዊ የቴሌቭዥን ስቱዲዮ ተጠናቆ በዛሬው እለት ተመርቋል።
በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃፍታይ ገብረ እግዚአብሔር እንደገለፁት ትክክለኛና ጥራትያለዉ መረጃን በወቅቱ ለህብረተሰቡ ማድረስ የተቋማት ኃላፊነት መሆኑን ጠቅሰዉ በጉለሌ ክፍለ ከተማ የተገነባው ይህ ዘመናዊ የቴሌቭዥን ስቱዲዮ ኃላፊነታችንን በተሻለ ደረጃ ለመወጣት የሚያስችል አቅም የሚፈጥር ነው ብለዋል።
አክለውም የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የዓለም የስህበት ማዕከል የሆነችውን አዲስ አበባን በማስተዋወቅ እንዲሁም ከቀሪው ዓለም ጋር በመረጃ በማስተሳሰር እየሰራ መሆኑን ጠቁመው ለዚህም የይዘት ለውጦች እየተደረጉና ከፍ ያሉ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።
ጉለሌ በታሪክና በተፈጥሮ ሀብት እጅግ የላቀ ድርሻ እንዳላት ያመለከቱት አቶ ሃፍተይ ፤ ዘመናዊ ስቱዲዮ መገንባቱ በዚህ በኩል ያለውን ፀጋ ለማስተዋወቅ እድል ይፈጥራል ብለዋል።
በኢትዮጵያ የተጀመረው የለውጥ ጉዞ ከግብ እንዲደርስ ከፍተኛ ሚና በመጫወት አሻራቸውን እያኖሩ ካሉ መካከል አንዱ የኮሙኒኬሽን ዘርፉ ነው በማለት ፤በከተማችን የጋራ ትናንትን ብቻ ሳይሆን የጋራን ዛሬ እና ነገን ለመገንባት ትልቅ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ገልጸዋል።
የጉለሌ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ በበኩላቸው ስቱዲዮው የክፍለ ከተማውን የኮሙኒኬሽን ሥራዎች ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር መሆኑን ገልጸው የህብረተሰቡን ጥያቄዎች በመሰብሰብ፣ የምሁራን ውይይቶችን በማዘጋጀት፣ የልማት ፕሮጀክቶችን በመዘገብ እና የተለያዩ የንቃተ ህዝብ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ረገድ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው አብራርተዋል።
አቶ ወልዴ አክለውም “በዲጂታል ዘመን የመረጃ ፍጥነትና ጥራት ወሳኝ ናቸው። ይህ ስቱዲዮ ለህብረተሰቡ የሚቀርቡ መልዕክቶች በሙያዊ መንገድ እንዲዘጋጁ እና እንዲሰራጩ ያግዛል” ብለዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.