ክረምቱን ቀድመን መዘጋጀት ያስፈልጋል!!
ዛሬ በአቃቂ ቃሊቲ ብዙ ጊዜ ለጎርፍ ተጋላጭ በሆነው ቦታ ላይ ጎርፍን የመከላከልና የአደጋ ዝግጁነት ስራን በይፋ አስጀምረናል።
አቃቂ ቃሊቲ በተፈጥሯዊ አቀማመጡ የአዲስ አበባ የታችኛው ክፍል በመሆኑ ከዚህ በፊት በጎርፍ አደጋ በተደጋጋሚ ተጠቂ ሲሆን ቆይቷል።
ዛሬ ለዚህ አካባቢ ቅድሚያ በመስጠት በሁሉም የከተማችን ቦታዎች ላይ ወንዞች ተፈጥሯዊ ፍሰታቸውን ጠብቀው እንዲፈሱ የተለያዩ ግንባታዎችን የመስራትና የፍሳሽ መስመሮችን የማፅዳት ንቅናቄን አስቀጥለናል።
ውድ የከተማችን ነዋሪዎችም የከተማ አስተዳደራችን እየሰራ ባለው የመከላከልና አደጋ እንዳያጋጥም የቅድመ ዝግጁት ስራ ላይ እድትሳተፋ እንዲሁም በየአካባቢያችሁ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮችን በማፅዳትና ቆሻሻን ወደ ፍሳሽ መውረጃ ባለመጣልና በአግባቡ በማስወገድ አካባቢያችሁን ከጎርፍ አደጋ እንድትጠብቁ ጥሪ አቀርባለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵየን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.