“ተስፋን እንትከል!

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

“ተስፋን እንትከል!

አረንጓዴ አሻራ የነገው ትውልድ ተስፋ!

ሀገራችን ኢትዮጵያ በተያዘው ዓመት 8 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ግብ አስቀምጣለች። 

ኢትዮጵያውያን  በየአመቱ አሻራቸውን ለማሳረፍ በጉጉት የሚጠባበቁት የአረንጓዴ አሻራ መረሃ ግብር፣  የሀገራችን የአረንጓዴ ልማት እና ዕጽዋት ሽፋን ከማሳደግ በተጨማሪ፣  የአየር ንብረት ለውጥን  በመከላከል በሰዎች አኗኗር ዘንድ ከፍተኛ ለውጥ እያመጣ ይገኛል፡፡
 
ኢትዮጵያውያን በየአመቱ በተደመረ አቅም በስኬት የሚከውኑት ይህ ፕሮጀክት፣ የደን መጨፍጨፍ ለመከላከልና የአካባቢን የአየር ሁኔታ ለማሻሻል ብሎም የተራቆተውን መሬት አረንጓዴ በማልበስ  የምግብ ሉኣላዊነትን ለመረጋገጥ፣ በተለይም  የአረንጓዴ ኢኮኖሚን በመገንባት ረገድ  ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡

ይህ ሀገራዊ ፕሮጀክት  የመሬት መራቆትን በመቀነስ፣ የአፈርና የውሃ ጥበቃ ሥራዎችን በማጠናከር የምግብና የውሃ ዋስትናን በማረጋገጥ፣ ኑሮን በማሻሻል እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም አቅምን በማሳደግ  የሀገሪቱን የወደፊት መልካም ዕጣ ፈንታ የሚያሳይ መሰረት እየጣለ ይገኛል፡፡

በዚህ  ስኬታማ ስራ  የአዲስ አበባ ከተማ የደን ሽፋን ከዚህ ቀደም ከነበረበት 2 ነጥብ ስምንት በመቶ ወደ 22 በመቶ  ደርሷል፡፡ የአረንጓዴ ሌላው ገፅታው፥ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ችግኝ ከማዘጋጀት እስከ መንከባከብ ባለው ሂደት ለበርካታቶች  የስራ ዕድል ተፈጥሯል፡፡ በዚህም የዜጎች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እየተሻሻለ መጥቷል፡፡ 

ተስፉን እንትከል!


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.