ለስፖርት መሠረተ-ልማት ልዩ ትኩረት በመስጠት የትውልድ የዘመናት ጥያቄን የመለሰችው አዲስ አበባ!
ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ ጎዳናዎች ለህፃናት፣ ለአዋቂዎችና ለወጣቶች ምቹ ያልነበሩ ተሽከርካሪ እና እግረኛ እኩል የሚጋፋባቸው ለአደጋ የተጋለጡ በተለይም በየመንደሩ የሚኖሩ ታዳጊዎች ኳስ ለመጫወት የተመቸ ቦታ ባለማግኝታቸው እራሳቸውን ለአደጋ አጋልጠው የተሽከርካሪን መንገድ ዘግተው ሲጫወቱ ማየት የተለመደ ነበር። ዛሬ ይህ ታሪክ ሆኖ አልፏል ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚሰራቸው ስራዎች ሁሉ ለታዳጊዎች ፣ ለወጣቶች እና ለህፃናት ምቹ ከተማን በመገንባት የከተማዋ ጎዳናዎች ለሁሉም ተስማሚ እንዲሆኑ ዘመን ተሻጋሪ ስራዎች አከናውኗል፡፡ በተለይም ለስፖርቱ ዘርፍ ልዩ ትኩረት በመሰጠቱ በማዘመንና ተደራሽነቱን በማስፋፋት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ 1,547 ደረጃቸውን የጠበቁ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች በመገንባት ለአገልግሎት አብቅቷል፡፡
እነዚህ መሠረተ ልማቶች፣ ነዋሪው በቅርበት ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን እንዲያከናውን በማስቻል የከተማዋን የስፖርት ገጽታ በከፍተኛ ደረጃ ቀይረውታል።
በተጨማሪም የአካል ብቃት እንቅስቃሴን የህይወት ዘይቤና ባህል በማድረግ ህብረተሰቡ በሚኖርበት፣ በሚማርበት እና በሚሰራበት አካባቢ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን በማዘውተር ጤናማና አምራች ዜጋ እንዲሆን እንዲሁም የጋራ ትውስታ (Shared Memories) እንዲኖረው አስችለውታል ።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.