ጎስቋላ ከባቢዋን የቀየረችው አዲስ አበባ!

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ጎስቋላ ከባቢዋን የቀየረችው አዲስ አበባ!

መዲናችን አዲስ አበባ፣ ዕድሜ ጠገብ ባለታሪክ ከተማ ብትሆንም፣ ስምና ዕድሜዋን የሚመጥን ዕድሳት ሳይደረግላት በመቆየቱ፣ መንደሮቿና መንገዶቿ የፈራረሱ ለዓይን የማይጥሙ፣ አፍንጫ የሚሰነፍጡ ሆነው ቆይተዋል። 

ይሁን እንጂ፥ ባለፈው ኣጭር ጊዜ በተሰራው ስኬታማ ስራ ከተማዋ ገፅታዋን እየለወጠች፣ የምትጀምራቸውን ፕሮጀክቶች በፍጥነትና በጥራት እያጠናቀቀች፣  ነዋሪዎቿን እያቀፈች፣ መስህቦቿን እያበዛች፣  የአፍሪካ የብልፅግና ፊት የመሆን ፅኑ መንገዷን ይዛ ትገኛለች፡፡

አዲስ አበባ፥ ውብ የቱሪስት መዳረሻዎችን በማስፋት ለዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ኩነቶች የምትመረጥ፣ ንፁህ፣ አረንጓዴ  ውብ ሥፍራን የተላበሰች፣ አሰራሯን ያዘመነች ህብረ ብሄራዊነቷን የጠበቀች ሰላም ያላት ውብ ከተማ መሆን ችላለች።

በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሰው ተኮር ልማቷ የብዙ ነዋሪዎቿን እንባ ያበሰች፣ መደገፊያ መጠጊያ የሆነች፣ ተስፋን የሰጠች የተጣሉትን ያስታወሰች ፣ የተራቡትን ያጎረሰች፣ የነገ ህፃናቶቿን የደገፈች፣ተማሪዎቿን ያስታወሰች፣ ማዕድ ያጋራች፣ የኑሮን ጫና ለማቃለል ሸክምን የተጋራች ፣ሌማት እንዲሞላ ያበረታታች እንደ አዲስ የተፈጠረች ከተማ ለመሆን በቅታች፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.