በተደራሽነትም ሆነ በተገልጋይ እርካታ ከፍተኛ ስኬት እያስመዘገቡ የሚገኙት የአዲስ መሶብ ማዕከላት
የ"አዲስ መሶብ" አንድ ማዕከላት ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት፡ ስራ ከጀመሩበት አጭር ጊዜ ጀምሮ ከ230 ሺህ በላይ ህዝብን በማስተናገድ 99 በመቶ የተገልጋዮች እርካታን አስመዝግበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማን የአገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን እና ለአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር የተወጠነው "አዲስ መሶብ" ፕሮጀክት ታላቅ ስኬት እያስመዘገበ ይገኛል።
እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ 11 ማዕከላትን ለመክፈት ታቅዶ እየተሰራ ሲሆን፣ እስከ ግንቦት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ 9ኙ ማለትም አራዳ፣ ቦሌ፣ ልደታ፣ ቂርቆስ፣ አዲስ ከተማ፣ ጉለሌ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ እና የካ ሙሉ በሙሉ ወደ አገልግሎት ማስገባት ተችሏል።
የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ደሳለኝ ተረፈ (ኢ/ር) እንደገለጹት፣ ቀሪዎቹ የአቃቂ እና የለሚ ኩራ ማዕከላት የግንባታ አፈጻጸማቸው ከ99.5 በመቶ በላይ በመሆኑ በቀጣይ ቀናት ተመርቀው አገልግሎት መጀመር የሚያስችላቸው ዝግጅት ተጠናቋል።
ማዕከላቱ ስራ ከጀመሩበት አጭር ጊዜ ጀምሮ ከ230 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ያስተናገዱ ሲሆን፣ በተደረገው ዳሰሳም የተገልጋዮች እርካታ 99 በመቶ መድረስ መቻሉን ገልጸዋል።
ይህ ስኬት ሊመዘገብ የቻለው በከተማ አስተዳደሩ ልዩ ድጋፍ የባለሙያ ቅጥር፣ ስልጠና እና መሰረታዊ ግብዓቶች ቀድመው በመሟላታቸው መሆኑንም ጠቅሰዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.