አዲስ አበባ የዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች የስህበት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አዲስ አበባ የዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች የስህበት ማዕከልነቷን እያረጋገጠች ትገኛለች!

ዛሬ ከጤና ሚንስትር ክብርት ዶ/ር መቅደስ ዳባ እና ከአፍሪካ በሽታዎች ቁጥጥርና መከላከል ማዕከል (Africa CDC)  ዋና ዳይሬክተር  ዶ/ር ዦን ካሴያ   ጋር በቀጣይ   ኖቬምበር  ወር ላይ ከተማችን አዲስ አበባ  5ኛውን አለምአቀፍ  የህብረተሰብ ጤና ኮንፈረንስ  ለማካሄድ መመረጥዋንና ኮንፈረንሱን በጋራ ለማዘጋጀት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬአማ ውይይት አድርገናል።

አዲስ አበባ በቅርብ ዓመታት ውስጥ በመሰረተ ልማት በሰራናቸው ስራዎች ፣ በነዋሪዎቻችን እንግዳ ተቀባይነት፣ሰላሟ የተረጋገጠ ከተማ በመሆኗ እና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች ለማካሄድ ምቹ ከተማ መሆን በመቻሏ  “የአፍሪካ የጤና ሉዓላዊነት እና ደህንነትን ማላቅ/...to advance Africa’s health soverignity and security agenda./ በሚል  5ኛውን ዓለምዓቀፍ የህብረተሰብ ጤና ኮንፈረንስ ለማዘጋጀት የሚያስችሉ ዝግጅቶች በስፋት በጋራ በመከናወን ላይ ነው፡፡

5ኛውን ዓለምዓቀፍ የህብረተሰብ ጤና ኮንፈረንስ የሃገራት መሪዎች ፣ሚኒስትሮች ፣የህብረተሰብ ጤና መሪዎች፣ፖሊሲ አውጭዎች ፣ተመራማሪዎች እና ባለድርሻ አካላትን የሚሳተፉበት ትልቅ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ነው ።

ፊጣሪ ኢትዮጵያና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.