በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚደረገው የስፖርት ፌስቲቫል በስኬት እንዲከናወን የሚመለከታቸው አካላት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡
በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚደረገውን የስፖርት ፌስቲቫል አስመልክቶ የፀጥታ ተቋማት አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቀው ወደ ስራ ገብተዋል፡፡
ፌስቲቫሉ በተያዘው እቅድ መሰረት ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አካላት ካደረጉት ዝግጅት በተጨማሪ የፕሮግራሙ አዘጋጆች እና ታዳሚዎች የሚኖራቸው ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ገልጿል፡፡
ስፖርት ወንድማማችነት እና አብሮነት ከሚገለፅባቸው ዘርፎች አንዱ መሆኑን ፖሊስ አስታውሶ ስፖርታዊ ፌስቲቫሉ የከተማችንን መልካም ገጽታ በሚገነባ እና ስፖርታዊ ጨዋነትን በተላበሰ መልኩ ሊካሄድ እንደሚገባ አሳስቧል፡፡
የፕሮግራሙ አዘጋጆች ከፀጥታ አካላት ጋር በጋራ እየሰሩ ነው፡፡ የዝግጅቱ ታዳሚዎች ፕሮግራሙ በሠላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ኃላፊነት ያለባችሁ በመሆኑ ከፖሊስ ጋር ተባብራችሁ መስራት ይጠበቅባችኋል፡፡ ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ ስለሚኖር ለፍተሻ መተባበር እና ወደ ፌስቲቫሉ ስፍራ የማይገቡ ቁሳቁሶችን ባለመያዝ ሁሉም ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል።
ፌስቲቫሉ በስኬት እንዲጠናቀቅ ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
ህብረተሰቡ ማንኛውም ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት በነጻ የስልክ መስመሮች 990፣ 991፣ 987፣ 816 እንዲሁም በ011-1-26-43-59፣ 011-5-52-63-02/03፣ 011-5-52-40-77፣ 011-5-54-36-78 እና 011-5-54-36-81 እንዲሁም በእጅ ስልኮች የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን (Citizen Engagement Application) EFPApp በመጠቀም ጥቆማ መስጠት እንደሚገባም ጥሪ ተላልፏል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.