ኢትዮጵያ ትመርጣለች ! የሕዝብ ሉዓላዊነት፣ የው...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ኢትዮጵያ ትመርጣለች ! የሕዝብ ሉዓላዊነት፣ የውሳኔ ሰጪነት መብት በተግባር ይረጋገጣል!!

ምርጫ የሕዝብ ሉዓላዊነት እውነተኛ መገለጫ፣ የዜጎች የባለቤትነት እና የውሳኔ ሰጪነት መብት በተግባር የሚረጋገጥበት ወሳኝ መድረክ ነው።

እውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚገነባውም፣ የሕዝብን ፍጹም ውሳኔ ሰጪነት በመቀበልና በማክበር ላይ ብቻ ነው። ሕዝብን "በምርጫ አትሳተፉ፣ አትምረጡ" በማለት ለማስፈራራት መሞከር፣ እንዲሁም “እኔ አውቅልሃለሁ" በሚል የተሳሳተ የሞግዚትነት መንፈስ የዜጎችን ነፃ ፈቃድ ለመቀማት መሻት ለሕዝብ ያለን ንቀት የሚያሳይ፣ ከዘመኑ የሕዝብ የፖለቲካ ንቃተ ሕሊና ጋር የማይሄድ ኋላ ቀር አካሄድ ነው።

ሕዝባችን ግን ከእነዚህ ሁሉ የተዛቡ የፖለቲካ አመለካከቶች እጅግ ልቆ የሄደ፣ የሚበጀውንና የማይበጀውን ጠንቅቆ የሚያውቅ፣ እንዲሁም የሀገሩን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በራሱ ሚዛናዊነት መወሰን የሚችል እጅግ አስተዋይና እውነተኛ ዳኛ ነው። ለዚህም አንዱና ዋነኛው ማረጋገጫ፣ ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች ከወዲሁ በንቃት በመመዝገብ የሀገራቸውን ብሩህ መጻኢ ዕድል ለመወሰንና የሚበጀውን ለመምረጥ ያሳዩት ከፍተኛ ዝግጁነትና ታሪካዊ ቁርጠኝነት ነው።

ስለሆነም፣ የሕዝብን ነፃ ምርጫ ማክበር የዲሞክራሲያዊነታችን መለኪያ ብቻ ሳይሆን የሀገራዊ ሕልውናችን እና የአንድነታችን ፅኑ መሠረት ነው። ይህ 7ኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ለሀገራችን ብቻ ሳይሆን፣ በመላው የአፍሪካ አህጉር የእውነተኛ ዲሞክራሲንና የሕዝብን የውስጥ አቅም በተግባር ለማሳየት የሚኖረው አዎንታዊ አንድምታ እና ምሳሌነት እጅግ የላቀ ነው።

#ኢትዮጵያ_ትመርጣለች #የሕዝብ_ሉዓላዊነት #ዲሞክራሲ
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.