ከዛሬ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም. (በጥሞና ወቅት) ጀምሮ ምን ምን ማድረግ አይቻልም?
1. በአካልና በዐደባባይ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች
ፖለቲካ ተኮር የሕዝብ ስብሰባዎችና ሠልፎች
የቤት ለቤትና የዐደባባይ ላይ ቅስቀሳዎች
የቅስቀሳ ኅትመቶችን እና ቁሳቁሶችን መለጠፍና ማሠርጭት
የቅስቀሳ አልባሳትን መልበስ
2. የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት
የቀጥታም ሆነ የተቀረጹ የዕጩ ወይም የፓርቲ ፕሮግራሞች ሥርጭት
የማኅበራዊ ትሥሥር ገጾችን በመጠቀም ቅስቀሳ ማድረግ
ፕሮጀክት ማስጀመር እና ማስመረቅ
"የጥሞና ጊዜን ማክበር የምርጫውን ተዓማኒነት ያረጋግጣል! መራጩም ያለ ምንም ውጫዊ ተፅዕኖ፣ ግርግርና ቅስቀሳ በሰላም አስቦ እንዲወሥን ይረዳል።"
የተረጋገጡ መረጃዎችን ይፋዊ የቦርዱን የፌስቡክ ገጽ እንዲሁም በሌሎች የቦርዱ የማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ አማራጮች አማካኝነት ማግኘት ይችላሉ ሲል ምርጫ ቦርድ አስታውቋል::
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.