በምሥራቅ ቦረና ዞን እየታየ ያለው የግብርና ትራ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በምሥራቅ ቦረና ዞን እየታየ ያለው የግብርና ትራንስፎርሜሽን፤ ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን ለመቻል ለምታደርገው ጉዞ ትልቅ ማረጋገጫ ነው!

በዚህ ወቅት ብቻ ታታሪ አርሶአደሮቻችን ከ176,223 ሄክታር በላይ መሬት በማልማት፣ ከ3.1 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚያገኙ ይጠበቃል። ከ101,000 በላይ አባወራዎችንና እማወራዎችን በማሳተፍና ዘመናዊ ትራክተሮችን በመጠቀም፣  በተደራጀ የክላስተር እርሻ አማካኝነት እምቅ አቅማችንን ወደ ምርታማነት እየቀየርን እንገኛለን። 

በምሥራቅ ቦረና ዞን ሊበን ወረዳ ከሚገኙት ሰፋፊ የስንዴ ክላስተሮች ጀምሮ እስከ ዋና ዋናዎቹ የጤፍ፣ የበቆሎ እና የቦሎቄ ምርቶች ድረስ የሚታዬው ውጤት፤ የሀገር ውስጥ የምግብ አቅርቦታችንን የማረጋገጥ ጉዞ ላይ ለመገኘታችን ህያው ምስክር ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.