በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት የተደረገው የላፍቶ ሆስፒታል በውስጡ ከያዛቸው በሰው ሠራሽ አስተውሎት የሚደገፉ እጅግ የረቀቁ መሣሪያዎች መካከል፦
👉 የቅድመና ድህረ ካንሰር ምርመራ ማሽን፦ በምሥራቅ አፍሪካ የመጀመሪያው የሆነ ሰው ሠራሽ አስተውሎት የተገጠመለትና የ2026 ምርት የሆነ የመጨረሻው ዲጂታል ቴክኖሎጂ
👉 በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው የሂሊየም ትነትን ሙሉ በሙሉ የሚያስቀር መሣሪያ
👉 ከአንድ የልብ ትርታ ባነሰ ጊዜ ሙሉ ምርመራ ማድረግ የሚችል ፈጣን የምርመራ ቴክኖሎጂ
👉 የልብና የደም ሥር ላቦራቶሪ፦ በቀጭን የደም ሥር በመግባት የልብና የአንጎል ደም ሥር ችግሮችን በአጭር ጊዜ ለይቶ የሚያክም የዘመኑ የመጨረሻ ጥበብ
👉 የጡት ካንሰርን በቅድሚያ ለመመርመርና በሁሉም አቅጣጫ የናሙና ምርመራ ለመውሰድ የሚያስችል የረቀቀ መሣሪያ
👉 ሙሉ በሙሉ ከሰው እጅ ንክኪ ነጻ የሆነ የሰውን ስህተት በማስቀረት ፈጣንና ጥራቱን የጠበቀ ውጤት የሚሰጥ በሀገራችን የመጀመሪያው የላቦራቶሪ ሥርዓት
👉 ዘመኑ የደረሰበት የመጨረሻው የቴክኖሎጂ ውጤት የሆኑ የአልትራሳውንድ እና የዲጂታል ማሽኖች
👉 በሰዓት 80 ሜትር ኩብ ኦክስጂን የማምረት አቅም ያለውና የሜዲካል ጋዝ ማምረቻ ፕላንት
👉 በብዙ ሆስፒታሎች የሚያጋጥሙ የኢንፌክሽን ችግርን ለማስቀረት የሆስፒታሉ ግድግዳዎችና ወለሎች ባክቴሪያን ሙሉ በሙሉ በሚከላከል ቁስ የተገነቡ ናቸው
👉 የማይቋረጥና ዘላቂ አገልግሎት ለመስጠት ሲባል የራሱ የውሃ ጉድጓድና የፍሳሽ ማጣሪያ ፕላንት የተገጠመለት
👉 ደረጃውን የጠበቀ 18 ዘመናዊ አስከሬን ለረጅም ጊዜ ማቆየት የሚያስችል ማቀዝቀዣን ጨምሮ በርካታ የህክምና ቴክኖሎጂዎችን ያካተተ ነው
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.