የላፍቶ ሆስፒታል ተመረቀ! ‎

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የላፍቶ ሆስፒታል ተመረቀ! ‎


‎በኢትዮጵያ በተሻሻለው የመከላከል እና አክሞ የማዳን የጤና ፖሊሲ መሠርት ፣ ሀገራችንን ቀዳሚ የህክምና ቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ፣ ለህክምና ወደ ውጭ ሀገር የሚወጣውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ለመቀነስ ለሰነቅነው ርዕይ እና መሰል የረቀቁ የዘርፉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ግንባታን ለማስቀጠል የላፍቶ ሆስፒታል አሻጋሪ ምዕራፍ ነው።

በ5.4 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ዘመናዊና ግዙፉ የላፍቶ ሆስፒታል እጅግ ዘመናዊ አቅሞች በመጠቀም እንደ ካንሰር፣ ውስብስብ የልብ ህመም እና ተያያዥ የህክምና ሁኔታዎችን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ህክምና የሚሰጥ ሲሆን፣ ዜጎች እዚሁ ሀገራቸው ውስጥ ልዩ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል። ይህ ታላቅ ተቋም የህክምና አገልግሎት አሰጣጥን ከመቀየር ባለፈ፣ ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፎች እራሷን ለመቻልና ለሀገራዊ ልማት ያላትን ጽኑ ቁርጠኝነት የሚያሳይ ህያው ምስክር ነው።

#EthiopiaDelivers

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.