ዛሬ 7ተኛውን የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አግልግሎት አዲስ ባለ 6 ወለል ህንፃ ገንብተን በቴክኖሎጂ አደራጅተን ለአገልግሎት ክፍት በማድረጋችን እንኳን ደስ አላችሁ!
ለዘመናት በተንዛዛ አሰራርና እጅ መንሻ እየተጠየቀበት ዜጎቻችንን ሲያማርር የነበረውን የመንግስት አግልግሎት አሰጣጥ ችግር ስርነቀል በሆነ መልኩ ለመፍታት በምንከተለው የመፍጠንና መፍጠር መርህ ፤ የአገልግሎት አሰጣጣችንን ቀልጣፋ፣ የዘመነና ፍትሃዊ ለማድረግ እንድ ብለን የጀመርነው መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አግልግሎት ለማህበረሰባችን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ቀንና ሌሊት በመስራት ዛሬ 7ኛውን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ማዕከል ለአግልግሎት ክፍት አድርገናል።
ህዝብ ወደ አገልግሎት መስጫ ቦታዎች በመሄድ ቀልጣፋ አገልግሎት ማግኘት ብቻ ሳይሆን፣ በተንቀሳቃሽ የአዲስ መሶብ አገልግሎት ይበልጥ ወደ ህዝቡ እንዲጠጋ በማድረግም ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ጀምረናል።
ለህዝባችን የገባነውን ቃል ለመፈፀም እንዲሁም የምናልመውን ብልጽግና እውን እንዲሆን ተከታታይነት ያለው የማያቋርጥ ተግባራትን እያከናወንን እንገኛለን።
ኑ በሚቀርባችሁ ማዕከል ያለምንም መንገላታት በመሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተጠቀሙ ማለት እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቧቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.