የከተማ አስተዳደሩ ሰው ላይ ቅድሚያ ሰጥቶ እየሰ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የከተማ አስተዳደሩ ሰው ላይ ቅድሚያ ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ

የከተማ አስተዳደሩ ሰው ላይ ቅድሚያ ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ሲሉ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ እና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ ተናገሩ።

400 የሚሆኑ በተስፋ ብርሀን የምገባ ማዕከላት ተጠቃሚዎች ከተረጅነት ወደ ስራ ፈጣሪነት ተሸጋግረዋል።

በሽግግር መርሀ ግብሩ የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ እና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለዜጎች ቅድሚያ በመስጠት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ወገኖችን በመመገብና በማቋቋም ወደ ስራ እያስገባ ይገኛል ብለዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ሰው ላይ ቅድሚያ ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ሲሉ አቶ ሚሊዮን ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ የሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጅት ደበላ የከተማ አስተዳደሩ በተስፋ ብርሀን የምገባ ማዕከላት ዜጎችን ከመመገብ ባለፈ በተለየያዮ ጊዜያት ከተረጅነት ወደ ስራ ፈጣሪነት ማሸጋገር ተቀዳሚ አላማው ነው ብለዋል።

በዛሬው ዕለትም 400 የሚሆኑ በማዕከላቱ ይጠቀሙ የነበሩ ዜጎች ከተረጅነት ወደ ስራ ፈጣሪነት መሸጋገራቸውን የጠቀሱት ወ/ሮ ቆንጅት፤ የምገባ ማዕከላቱ የጥገኝነት ማሳያ ሳይሆኑ መሸጋገሪያ ድልድዮች ናቸው ሲሉ ገልፀዋል።

ተጠቃሚዎቹ ከመስሪያ ቁሳቁስ ባለፈ መንቀሳቀሻ እንዲሆናቸው የገንዘብ ድጋፍ እንደተደረገላቸው ተመላክቷል።

ዛሬ ከተረጅነት ወደ አምራችነት የተሸጋገሩ ተጠቃሚዎች የከተማ አስተዳደሩ እያከናወነ ያለው ተግባር በህይወታችን ላይ ለውጥ አምጥቷል ያሉ ሲሆን፤ ለዚህ ተግባርም ምስጋናቸውን አቅርበዋል


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.