የሀገራችን፣ የከተማችን ኩራት እና ውበት የሆኑ ህዝባዊ መሰረት ያላቸውን ክለቦች መደገፍ ውዴታ ሳይሆን ግዴታ ነው። - ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የከተማችን አርማ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ኩራት ጠንካራ ህዝባዊ መሰረት እና ድጋፍ ካላቸው እንቁ ክለቦች መካከል እና በቅርቡ ውስጣዊ ችግር ያጋጠመው አንጋፋው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ይበልጥ ለማጠናከርና ዘመኑን የዋጀ ጠንካራ ተቋም ለመገንባት በተዘጋጀው ጉባኤ ላይ በመገኝቴ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል።
የነበሩ ጥንካሬዎች ይዞ የነበሩ ክፍተቶችን ሞልቶ ወደፊት ለመራመድና በትውልድ መካከል የማይበጠስ ድልድይ ለመስራት ጠንካራ ተቋም መሰረት ነው። ስለሆነም የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ከገጠሙት ፈተናዎች ሁሉ በፅናት እንዲወጣና ታሪካዊ ክብሩን ጠብቆ እንዲቀጥል የከተማችን አስተዳደር አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ሲያደርግ ቆይቷል፤ በቀጣይም ይህ ድጋፋችን ይበልጥ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።
መሰል ድጋፎች ለቅድስጊዮርጊስ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ህዝባዊ ክለቦች የእኛን ድጋፍ በፈለጉ ጊዜ ሁሉ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። ምክንያቱም እግርኳስ በከተማችን እጅግ ተወዳጁ ስፖርት ከመሆን ባለፈ አብሮነታችንን፣ አንድነታችንን እና ወንድማማችነታችንን የምናጠናክርበት፣ የህዝብ ለህዝብ ትስስራችንን የምናሳድግበት ትልቅ መሳሪያ ነው።
በከተማችን እየገነባናቸው ያሉ ዘመናዊ የስፖርት መሰረተ-ልማቶች፣ የምናስተናግዳቸው ታላላቅ ውድድሮች እና የምንፈጥረው የስፖርት ባህል “የስፖርት ቱሪዝምን” (Sports Tourism) ለማሳደግ ለጀመርነው ስራ ትልቅ ስንቅ ናቸው።
ክለቦቻችን ሲጠነክሩ የከተማችን ገፅታና ቱሪዝም አብሮ ያድጋል።ስለሆነም ለክለባችሁ ዳግም ውጤታማነት ላሳያችሁት ህብረት እና ቁርጠኝነት ምስጋናዬ የላቀ ነው።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.