በበጎነት መንደር
ዛሬ በኮልፌ ቀራንዩ እና የካ ክፍለ ከተሞች በበጎነት መንደር ያስገነባናቸውን አራት G-5 የሆኑ ህንፃዎች (በኮልፌ ቀራንዮ 72 ቤቶች፤ በየካ 78 ቤቶች) አጠቃላይ 150 ቤቶች ለአቅመ ደካሞች፣ ማህበራዊ ችግር ውስጥ ላሉና ለሃገር ባለውለታዎች አስተላልፈናል።
ለተጠቃሚዎቹ ያስተላለፍነው ቤት ብቻ ሳይሆን በጥራት የተገነቡ የህፃናት ማቆያ /ዴይ ኬር/፣ ህፃናት ቦርቀው የሚጫወቱባቸው መጫወቻዎች፣ ወጣቶች ተስጥኧቸው የሚያወጡባቸው የስፖርት ሜዳ እና ለነዋሪዎች በተመጣጥኝ ዋጋ የሚያቀርቡ የሸማች ሱቆች የተሟሉላቸው፣ ማህበራዊ ፍትህን የሚያነግሱ ንፁህ መኖሪያ መንደሮች ናቸው።
እነዚህን የበጎነት መንደሮች በጥራትና በፍጥነት ተገንብተው እንዲጠናቀቁ በክትትል እና ድጋፍ አስተዋጽኦ ላደረጋችሁ አመራሮች እና ሰራተኞች እንዲሁም በገንዘባችሁ ድጋፍ ላደረጋችሁ ልበቀናዎች በነዋሪዎቹ ስም ከልብ አመሰግናለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.