አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት እናደርጋታለን ብለን ስንነሳ በአካልና በአዕምሮ የዳበረ ትውልድ መገንባትን ቅድሚያ በመስጠት ነው።
በቦሌ ክፍለ ከተማ 5 ስፖርት ማዘውተሪያዎችን፣ 95 የህጻናት መጫዎቻዎችን፣ 6 የህጻናት ማቆያዎችን (day cars )፣ ካፍቴሪያዎችን፣ አንፊ ትያትሮችን እንዲሁም በርካታ የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጡ መሰረተ ልማቶችን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል ።
በተለይ ካፒቴን አበራ ለሚ ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የገነቡልን በ4,900 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው ስታዲየም የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳ፣ የመሮጫ ትራክ፣ ጥላ ያለው የተመልካች መቀመጫ፣ ለወጣቶች የስራ እድል የሚውሉ ሱቆች፣ መታጠቢያና መጸዳጃ ቤቶች፣ ጂምናዚየም እና የእቃ ማከማቻ መጋዘንን ያካተተ ነው።
የለሚ ኮሚኒቲ ስታዲየምን ገንብተው ያስረከቡንን ካፒቴን አበራ ለሚን በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም እያመሰገንኩ የአካባቢው ነዋሪዎችም ስታዲየሙን በእንክብካቤ እንድትጠቀሙበት አሳስባለሁ።
የክፍለ ከተማዉ አመራሮችም ለሰራችሁት ድንቅ ስራ ምስጋና ይገባችኋል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.