ትላንት ምሽት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ 18 ሄክታር ቦታ ላይ የተገነባውን የወንዝ ዳርቻ እና ፓርክን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል ።
ፓርኮቹ የእግረኛና የብስክሌት መንገዶችን እንዲሁም ድልድዮችን፣ የተለያዩ 6 ስፖርት ማዘውተሪያዎችን ፣ 7 የህጻናት መጫዎቻዎችን ፣አረንጓዴ ስፍራና የአትክልት አጸዶችን፣ 6 ካፍቴሪያዎች፣ 3 አንፊ ትያትሮችን እና ልዩ ልዩ መናፈሻዎችን እንዲሁም በርካታ የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጡ መሰረተ ልማቶችን ያካተቱ ናቸው።
ይህም በሁሉም ደረጃ የሚካሄዱ የልማት ስራዎቻችን አካታች እና ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል እንደፍላጎቱ የሚጠቀምባቸው እንዲሆኑ የያዝነው አቅጣጫ ማሳያ ነው።
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አመራሮች እና ነዋሪዎች በጋራ ለሰራችሁት ድንቅ ስራ በጣም እናመሰግናለን ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.