በዛሬ እለት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ3 ሄክታር መሬት ላይ የተገነባውን እና 18 ሱቆችና 18 ሼዶችን ያካተተ የተቀናጀ የከተማ ግብርና ማዕከል አገልግሎት አስጀምረናል ።
ከተማችን ለሁሉም የምትመች የጋራ ቤታችን ናት ልማታችንም አካታች ነው። ባለፈው ስርዓት ውስጥ አርሶ አደሩ የሚገፋበት መሬቱ ብቻ ተፈልጎ የሚዘነጋበት በመሆኑ ለለውጡ መምጣት ገፊ ምክንያት ሆኗል።
አርሶ አደሩ በሁሉም የከተማ ልማት ዉስጥ አካተን አብሮ እንዲለማ እና ተጠቃሚነቱ እንረጋገጥ ከማድረግ ባሻገር ለልማት ሲነሳ ተገቢውን ካሳ ከማግኘት ባለፈ ከልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከዚህን በፊት በአቃቂ ቂሊቲ ክፍለ ከተማ 14ሺ ሄክታር የተቀናጀ የግብርና ምርቶች ልህቀት ማዕከልን የገነባን ሲሆን ዛሬ በለሚ ኩራ የመረቅነውም የዚሁ አካል ነው።
እነዚህን መሰል ማዕከላት በሌላ በኩል የከተማው ነዋሪ የሚያጋጥመውን የዋጋ ንረት ለመከላከል እና በተመጣጣኝ ዋጋ የግብርና ምርቶችን ለማቅረብ የሚያስችል ነው ይህን መሰሉ አሰራር በጋራ ማደግን ተባብሮ መበልጸግን የሚያሳድግ ነው።
ይህንን ስራ በማቀድ፣ በማስተባበር ውጤታማ ላደረጉ ሁሉ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.