ትውልዱ ገብቶታል !!

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ትውልዱ ገብቶታል !!

 

የዛሬው የወጣቶች ድጋፍ እና ተነሳሽነት እጅግ አስደናቂ ነበር። እኛ ለኢትዮጵያ ብልጽግና በትጋት ስንሰራ፣ ወጣቱ ደግሞ የዚህ ስራ ፍሬ ተቋዳሽ እና የሀገሪቱን ብልጽግና የሚያጣጥም ይሆናል።

በአሁኑ ወቅት ሀገራቸውን የሚወዱ እና ኢትዮጵያን  ከፍ ለማድረግ የሚተጉ ወጣቶችን መመልከት፣ እኛም በበለጠ ትጋት እንድንሰራ ትልቅ መነሳሳትን ይፈጥርልናል።

ከዛሬው በተጨማሪ ሌላው ማሳያ፣ ሰሞኑን አዶናይ ብርሃነን የመሳሰሉ  ወጣቶች      እንደነ ዲላን ፔጅ ያሉ ታዋቂ የአጫጭር ማህበራዊ ሚዲያ ዜና አቅራቢዎችን ወደ ሀገራችን በማምጣት የኢትዮጵያን በጎ ገፅታ ለመገንባት እያከናወኑት ያለው ተግባር የሚበረታታ እና ይበል የሚያሰኝ በመሆኑ፣ ወጣቶቹን “በርቱ!” ልንላቸው ይገባል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.