የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፉት ጥቂት ዓ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፉት ጥቂት ዓመታት በትምህርትና በጤናው ዘርፉ የለውጥ አቢዎት አካሂዷል አቶ ጃንጥራር አባይ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፉት ጥቂት ዓመታት በትምህርትና በጤናው ዘርፉ የለውጥ አቢዎት አካሂዷል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ተናገሩ።

አቶ ጃንጥራር በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የተሰሩ የተለያዮ ፕሮጀክቶችን አስመርቀዋል።

ላለፉት አምስት ዓመታት ያለምንም እረፍት ስኬታማ ስራዎችን ሰርቷል ያሉት አቶ ጃንጥራር፤ በተለይም በትምህርት ላይ በተሰራው ስራ ህፃናት ከልጅነታቸው ጀምሮ ብሩህ አዕምሮ ኖሯቸው አድገው ለሀገር ጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል ሲሉ ገልፀዋል።

በጤናው ዘርፍም እንደ ከተማ በተሰሩ ስራዎች ጤና ጣቢያዎችን በመገንባት፣ አቅማቸው እንዲያድግ ከማድረግ ባለፈ ሆስቲታሎችም ደረጃቸውን እንዲጠብቁ ተደርገዋል ብለዋል።

የቄርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ምስክር ነጋሽ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በክፍለ ከተማው በተለያዮ ወረዳዎች የተመረቁ 8 ፕሮጀክቶች ከ420 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገባቸው መሆኑን ተናግረዋል።

የቄርቆስ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎችም ዛሬ የተመረቁት የልማት ስራዎች ችግር ፈችና የህዝቡን ጥያቄ የመለሱ ናቸው ብለዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.