ዛሬ ለከተማች ተጨማሪ የሆነ አዲስ ኢኮ ሁለገብ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ ለከተማች ተጨማሪ የሆነ አዲስ ኢኮ ሁለገብ የህዝብ መዝናኛ ፓርክ መርቀን ለአግልግሎት ክፍት እድርገናል።

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ አስኮ አዲስ ሰፈር በ30,ቪህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ፥ ለህጻናት፥ ለወጣቶች፥ ለአረጋውያን፥ ድሃ ሃብታም ሳይል አካታች ሕዝብ በጋራ የሚገለገልበት ውብና ማራኪ ሆኖ የተጠናቀቀው ሁለገብ የመዝናኛ ፓርክ ለአካባቢው ነዋሪዎች አማራጭ የመዝናኛ ቦታ ሆኖ የሚያገለግል ነው ።

ፓርኩ በውስጡ ፋውንቴይን፥ የእግር ኳስ ሜዳ:፥ የህጻናት መጫወቻ ፥ አምፊ ቲዓትር፥ ዘመናዊ ካፍቴሪያ : ሱቆች: የጁስ ባር፥ ፓርኪንግ፥ ዘመናዊ ሻወር እና መፀዳጃ ቤት እንዲሁም ሰፊ የእግር ጉዞ የሚደረግበት መንገድ ተሟልተውለት በጥራት ተገንብቶለታል።

ቦታው ከዚህ በፊት የቆሻሽ መጣያ የነበረ፥: ህገ ወጦችንም አለ አግባብ ይጠቀመበት የነበረ ሲሆን፥ ዛሬ በርካታ እሴቶች ተጨምረውበት መንፈስን የሚያድስ፥ ህዝብ በጋራ የሚጠቀምበት፥ ንፁህ አካባቢን ፈጥሯል ።

ይህንን ሁለገብ የመዝናኛ ፓርክ ሁላችሁም እየተጠቀማችሁበት እንድትንከባከቡት አደራ እላለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.