የአብሮነት እሴቶቻችንን በግብር እየተገበረች ያ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአብሮነት እሴቶቻችንን በግብር እየተገበረች ያለች ውብ ከተማ ፥ አዲስ አበባ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በከተማዋ ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራባቸዉ ዘርፈ-ብዙ የልማት ስራዎች አንዱና ዋነኛው፥ ሰዉን ማዕከል ያደረጉ ሰዉ ተኮር ስራዎች ናቸዉ፡፡

ከሰዉ ተኮር የልማት ስራዎች መካከል፥ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በከተማችን በተለያዩ ማህበራዊ ጫናዎች ምክንያት ለችግር የተጋለጡ አረጋውያንን፣ አቅመ ደካሞችን እና የሃገር ባለዉለታዎችን በሁሉም ክፍለ ከተሞች በማሰባሰብ በ29 የምገባ ማዕከላት በቀን ሁለት ጊዜ ትኩስ፣ ጤናማ እና የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ በማድረግ ከተማ አስተዳደሩ ለህዝብ ያለዉን ፍቅር እና ክብር በተግባር እያረጋገጠ አሁንም አጠናክሮ እየቀጠለ ይገኛል።

በማየትኞቹም የመዲናዋ የልማት ስኬቶች ጎለተዉ የሚታዩ እነዚህ ሰዉ ተኮር የልማት ስራዎች፣ የነበሩንን የአብሮነት እሴቶቻችንን ይበልጥ ከማጠናከር እና የስራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር፣ ለሁለተናዊ እድገታችን ትርጉም ያለዉ ለዉጥ በማምጣት የዜጎችን ማህበራዊ፣ ስነ-ልቦናዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በመቅረፍ የበኩላቸዉን ሚና እየተወጡ ይገኛሉ፡፡

በከተማችን ድህነትን ለመቀነስ እና ማህበራዊ ፍትህን ለማንገስ እንዲሁም ሁለተናዊ ፈጣን እድገት ለማምጣት የሚሰሩ እነዚህ ሰዉ ተኮር የልማት ስራዎች፣ በምድራዊዉ ብቻ ሳይሆን በመንፈሳዊዉ ዓለም ጭምር ዋጋቸዉ የላቀ ነዉና በተጀመረዉ የልማት ጉዞ አሁንም በቁርጠኝነት ይቀጥላል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.