የኢትዮጵያ ልኡካን ቡድን በ13ኛው ዓለም-ዓቀፍ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የኢትዮጵያ ልኡካን ቡድን በ13ኛው ዓለም-ዓቀፍ የከተሞች ፎረም ላይ በባኩ፣ አዘርባጃን እየተሳተፈ ይገኛል።

ፎረሙ፥ “ቤት ለሁሉም፤ ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ጠንካራ  ከተሞች እና ማህበረሰቦች” በሚል መሪ ሐሳብ እየካሄደ ሲሆን፤ ዓለም አቀፋዊ የመኖሪያ ቤት ችግርን መፍታት፣ ዘላቂ የከተማ ልማት፣ ጠንካራ እና ሁሉን አቀፍ ከተሞች፣ የአየር ንብረት እና የመኖሪያ ቤት ግንኙነቶች፣ መልሶ ግንባታ እና ተመጣጣኝ የመኖሪያ ቤት የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ይመከርባቸዋል፤ ልምድ ልውውጥ እና የመስክ ጉብኝትም ይካሄዳል። 

ቡድኑ ከውይይቶች እና የመስክ ጉብኝቶች በተጨማሪ፣ የሀገራችን  ኢትዮጵያን ብሎም የመዲናችንን አዲስ አበባ ገፅታ ለዓለም ማስተዋወቅ የሚችል እና በዛሬው ዕለት በተከፈተው ኤክስፖ መንግስት ከግል ዘርፍ ጋር በመተበበር ሀገራችን ኢትዮጵያን የሚገልፅ ፓቪልዮን (ቡዝ) በመውሰድ በተለያዩ መንገዶች የተዘጋጁ መረጃዎች በፅሁፍ፣ ቪድዮ እና Virtual Reality (VR) ወዘተ. በመጠቀም ሰፊ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.