የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አስርት ዓመታት ለሚመዘገበው ዕድገት መሠረት የሚሆን የሉዓላዊ ዲጂታል መሠረተ ልማት እየገነባች መሆኗን አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ''የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነጻነት'' በተሰኘው ሀገራዊ ጉባኤ ላይ በሰጡት ማብራሪያ ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አስርት ዓመታት ለሚመዘገበው ዕድገት መሠረት የሚሆን የሉዓላዊ ዲጂታል መሠረተ ልማት እየገነባች መሆኗን አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል።
እንደ ግብርና፣ ጤና፣ ፋይናንስ፣ ትምህርት እና ኢነርጂ ያሉ እያንዳንዱ ዘርፎች አሁን ላይ በሀገር በቀል የክላውድ ቴክኖሎጂ የሚቀነባበሩ፣ በሀገር ውስጥ የሚመሩ እና በኢትዮጵያ ቋንቋዎች መግባባት ለሚችለው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ግብዓት የሚሆኑ ተግባራዊ መረጃ ምንጮች ሆነዋል። ዳይሬክተሩ እንደገለጹት፤ "የራሳችን መረጃ ከሌለን የኛ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ባዕድ ይሆናል፤ የራሳችን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ከሌለን ደግሞ መረጃዎቻችን ይባክናሉ።
"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ይህንን ክፍተት ለመሙላት የተቀረጸ ብሔራዊ ስትራቴጂ ሲሆን፤ ይህም ሉዓላዊ የክላውድ ዳታ ሴንተርን፣ ብሔራዊ የዳታ ሌክ ሀውስን እንዲሁም በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ፣ በትግርኛ እና በሶማሊኛ ቋንቋዎች የሰለጠነ እና ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ቁጥጥር ስር የሚመራ ሀገር በቀል ላርጅ ላንግዌጅ ሞዴልን መገንባትን ያካትታል። በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ቀዳሚ እየሆኑ ያሉት ሀገራት መረጃቸውን ወደ ምርታማነትና ወደ አዲስ የኢኮኖሚ እሴት እየቀየሩ ያሉ ናቸው፤ ኢትዮጵያም አሁን ላይ ይህንኑ መሠረት እየገነባች ትገኛለች ብለዋል።
#PMOEthiopia #EthiopiaDelivers
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.