በፕላንና ልማት ሚኒስቴር የዕቅድ ክትትልና ግምገማ ዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዘሪሁን ከበደ
በፕላንና ልማት ሚኒስቴር የዕቅድ ክትትልና ግምገማ ዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ዘሪሁን ከበደ እንደገለፁት፤ የኢትዮጵያ ዲጂታል ሉዓላዊነት አሁን ላይ ከርዕይነት ባለፈ በተግባር ላይ የዋለ መሠረተ ልማት ሆኗል። ይህ የዲጂታል ዕቅድ ክትትልና ግምገማ ሥርዓት እያንዳንዱን ብሔራዊ አመላካች፣ የሪፎርም ፕሮግራም እና የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን ቁልፍ የአፈጻጸም አመላካቾች በአንድ በተረጋገጠ ብሔራዊ መድረክ ላይ እንዲመሩ ያደርጋል። በዚህ ሥርዓት ውስጥ የሚገኘው አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በፌዴራልና በክልል ተቋማት ውስጥ ከሚገኙና ከጸደቁ ብሔራዊ መረጃዎች ላይ በመነሳት፣ የመረጃ ምንጮችን በመጥቀስ አሁናዊ ምላሾችን ይሰጣል። በመሆኑም የተበታተነ መረጃ እና የዘገየ ውሳኔ አሰጣጥ የነበረው የአመራር ፈተና አሁን ላይ ታሪክ ሆኗል።
ሥርዓቱ ተገንብቶ ተጠናቋል፤ የአመራርና የክትትል ማዕቀፉም ሥራ ላይ ውሏል፤ የተመዘገቡት ስኬቶችም ተጨባጭ ናቸው። ይህም ለእያንዳንዱ ቁጥር አንድ የታመነ የመረጃ ምንጭ መኖርን፣ ሙሉ ተጠያቂነትንና የኦዲት ዐሻራን ከማረጋገጡም በላይ፣ አመራሩ ጊዜ ያለፈባቸው ሪፖርቶች ላይ ሳይሆን በወቅታዊ መረጃዎች ላይ ተመስርቶ ውሳኔ እንዲያስተላልፍ አስችሎታል። ቀጣዩ ምዕራፍ የእያንዳንዱ ተቋም ኃላፊነት ይሆናል፤ ይህም ከዚህ አንድ ወጥ ብሔራዊ ሥርዓት ጋር መገናኘት፣ ሥርዓቱን ተግባራዊ ማድረግ እና በዛም አማካኝነት መምራትን ያጠቃልላል።
#PMOEthiopia #EthiopiaDelivers
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.