አትለምኑ ማለት ነውር አይደለም። ይልቅ ነውር የ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አትለምኑ ማለት ነውር አይደለም። ይልቅ ነውር የሚሆነው በተቃራኒው ጎዳና ወጥቶ መለመንን የሚያበረታታው ነው።

 

ኑ አትለምኑ የተዘጋጀውን ተጠቀሙ ማለት፤ ጎዳና ላይ ወጥቶ ከመለመን ጋር በማንኛውም መመዘኛ  ሊነፃፀር እይችልም።

ልመናና የሚያበረታታ ፣መቼም ከአስተሳሰብ ብቻም ሳይሆን አስተዳደግንም ጭምር ሊገልፅ ካልሆነ በቀር።

በተለይ በአሁን ወቅት ፥ በዓለም ሁሉ የኑሮ ውድነት በጦዘበት፤ የትኛውም ዓለም ላይ ሁሉንም ነገር ሙሉ  ሆኖ አያውቅም። ሁላችንም በምንኖርበት የዓለም ጫፍ የምናየው ሃቅ ስለሆነ።

አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ምንም የምገባ ፕሮግራም  ካልነበረበት ዛሬ 29 የምገባ ማዕከላትን ከፍተን  አቅም የሌላቸውን በየቀኑ መመገብ ማለት የህዝብን እዉነተኛ ችግር ለሚረዳ ሊበረታታ  እንጂ  ሊራከስ የሚገባ ተግባር አይደለም። 

ለማህበራዊ ችግር የተጋለጡ፣  ጧሪ እና ጠያቂ ለሌላቸዉ አረጋዊያን ጎዳና ላይ ከምትለምኑ፥ ኑ በተዘጋጁት ማዕከላት በቂ ፣ንፁህና ትኩስ ምግብ አለ፥ ኑ በክብር ተመገቡ ማለት ነውር አይደለም። ይልቁኑ ነውር የሚሆነው በተቃራኒው ለማህበራዊ ችግር ለተጋለጡ ሰዎች አንድ ችግር የሚያቃልል ነገር ሰርተዉ ወይ ረድተዉ  የማያዉቁ  ሰዎች   ከምገባ ማእከል ከምትበሉ ጎዳና ውጡና  ለምኑ እያሉ ለፓለቲካ ንግድ ማዋሉ ነዉ ። 

የጎደለም ካላ፥ ምን ላግዝ፥ እኔ ይህንን ማገዝ እችላለሁ ማለት ለወገን ማሰብ  ይገባ ነበር።

ከቀልብ መሆን ጥሩ ነው ። ከሰውነት መውረድ ማለት በተቸገሩት ላይ መቀለድ ሲጀመር ነው።

ለነገሩ  ቢሳለቁ አይፈረድባቸዉም  ።እነሱ በአብዛኛዉ ያሉት ባህር ማዶ  ለማህበራዊ ችግር የተጋለጡ ሰዎች  የት እንዳሉ? እንዴት ወለዉ እንዳደሩስ የት ያዉቁና !

ፕሮግራሙን ደግፋችሁ አብራችሁን ደሃን እየመገባችሁ ላላችሁ ባለሀብቶች ሁሉ ፈጣሪ አምላክ ይባርካችሁ!!


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.