ዛሬ ያስመረቅነው የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክን...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ ያስመረቅነው የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊ መቻልን ማሳያ ጭምር ነው !

 

በ93.9 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈውና ዛሬ በይፋ የመረቅነው የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ፣ የከተማችን እና የሀገራችን የኩራት ምንጭ ነው። 
ይህን ግዙፍ የኢንዱስትሪ ፕሮጀክት ልዩ የሚያደርገው ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያዊያን ዲዛይነሮች፣ አርክቴክቶችና መሐንዲሶች፣ አመራሮች፣ የጉልበት ሠራተኞች እና ማኅበራትን ጨምሮ  በእኛው በኢትዮጵያውያን እጅ እና ላብ እውን የሆነ፣ ደረጃቸውን በጠበቁ ህንፃዎች መገንባቱ እንዲሁም ያለ አንዳች ብድር በከተማችን በጀት እውን መሆኑ ነው። 

መለስ ብለን የቀደሙትን በኢትዮዽያ የተገነቡትን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ስንመለከት፣  በውጭ ሀገር ብድር እና አሁን ካወጣነው በብዙ እጥፍ በሚበልጥ ወጪ  በውጭ ድርጅቶች በሼድ ደረጃ የተገነቡ ነበሩ ። 
በገላን ጉራ የኢንዱስትሪ ፓርክ  ይህንን ታሪክ ቀይረናል! በራሳችን አቅም፣ በራሳችን ባለሙያዎች፣ በራሳችን በጀት መሥራትና ማሳካት እንደምንችል በተግባር አረጋግጠናል።

አዎ! ዛሬ ያስመረቅነው ሕንፃን እና ማሽኖችን ብቻ አይደለም፤ መቻልንም ነው! 

ለዚህ ስኬት ሌት ተቀን የደከማችሁ በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.