ዛሬ የከተማችንን ኢኮኖሚ የሚያሳድግና ለበርካታ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ የከተማችንን ኢኮኖሚ የሚያሳድግና ለበርካታ ዜጎች የተስፋ በር የሚከፍት ታላቅ የምስራች ይዘን ቀርበናል፤ የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ የግንባታ ስራን በስኬት አጠናቀን በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን አስመርቀናል።

ዛሬም የረዳን ፈጣሪ  ይመስገን !
እንኳን ደስ አላችሁ !

መዲናችን አዲስ አበባ፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ልማት ከከተማዋ ስትራቴጂካዊ ዕድገት ጋር በማቀናጀት ረገድ አዲስ ምዕራፍ እየከፈተች ትገኛለች። በከተማችን እየተመዘገቡ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስኬቶች የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ከመሰረቱ ከማሻሻል ባለፈ፣ የከተማዋን ገጽታና መልክ በመቀየር፣ ሰፊ የስራ ዕድሎችን በመፍጠርና ማህበረሰባችንን የላቀ ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ ተኪ  የማይገኝለት ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እያስመዘገቡ ይገኛሉ።

የከተማ አስተዳደራችን ዋነኛ የኢኮኖሚ ሞተር የሆኑትን እነዚህን የኢንዱስትሪ መንደሮች በማስፋፋት፣ የስራ ቦታዎችን በማዘመንና አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል በማድረግ ሀገራዊ አበርክቷቸው እንዲጎለብት በልዩ ትኩረት እየሰራ ይገኛል። ዛሬ ለምረቃ የበቃውና ለታላቅ አገልግሎት ዝግጁ የሆነው የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለዚህ ቁርጠኝነታችን  አይነተኛ ማሳያ ነው።
 
የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ፣ 93.9 ሄክታር ላይ ያረፈ ሲሆን  
•  ለ20 ሺህ ሰዎች የስራ እድል መፍጠር የሚችል፣ 
•  116 የማምረቻ ቦታዎች ያሉት፣
•  ምቹ እና ሰፋፊ የምርት  ማከማቻና ማሳያ መጋዘኖች ያሉት፣
•  356 ቢሮዎች ያሉት፣
•  248 ሱቆች  ያሉት፣
•  ሆቴል እና ካፍቴሪያ፣
•  በአንድ ጊዜ ከ400 በላይ መኪና ማቆም የሚችል ፓርኪንግ ያለው፣ 
•  10 ትራንስፎርመሮችና ዘመናዊ ጀነሬተሮች የተገጠመለት፣
•  4 ኪሎ ሜትር የአስፓልት መንገድ   የተሰራለት፣
•  25 የሰው እና የእቃ ማጓጓዣ ሊፍት የተገጠመለት፣ 
•  ዘመናዊ   የቴክኖሎጂ ግባአቶችንና የእሳት አደጋ መከላከያ የተሰራለት፣ 
•  ራሱን የቻለ  የውሃ ጉድጓዶች ያለው፣
•  እንዲሁም የጋራ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ያሉት ሲሆን፤ ከነዚህም ውስጥ ፤
•  የጥራት ቁጥጥር
•  ዘመናዊ የቆሻሻ ማጣሪያ ሥርአት የተሟሉለት 
•  ሰፊ የአረንጓዴ ስፍራዎች  እና የመዝናኛ ስፍራዎች የተሟሉለት  
•  በተጨማሪም የህጻናት ማቆያ እና  የስፖርት ሜዳ የተገነባለት
በአጠቃላይ ዘመናዊና ሁለገብ የኢንዱስትሪ ፓርክ ነው፡፡

ይህ ግዙፍ የኢንዱስትሪ ፓርክ ለሀገራችን የኢኮኖሚ ዕድገት አዲስ መነቃቃትን የሚፈጥር ታላቅ የልማት አሻራችን ነው። ፕሮጀክቱ በተቀመጠለት ጊዜ፣ ጥራትና በጀት ተጠናቆ ለዚህ ታላቅ ስኬት እንዲበቃ ሌት ተቀን የደከማችሁ፣ ያስተባበራችሁና የደገፋችሁ በየደረጃው ያላችሁ አመራሮችና ባለሙያዎች፣ የወገን አለኝታነታችሁን ያሳያችሁ የአካባቢው ማህበረሰብ፣ እንዲሁም ግንባታውን በታማኝነትና በብቃት ላከናወናችሁ ኮንትራክተሮችና ማህበራት  የሥራ ተቋራጮች በሙሉ፣ በከተማ አስተዳደሩና በራሴ ስም ልባዊ ምስጋናዬንና አክብሮቴን አቀርባለሁ። በርቱ፣ እጅግ ኮርተንባችኋል!"

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.