ቃልን በተግባር ይቀጥላል

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ቃልን በተግባር ይቀጥላል

ዛሬ ማለዳ በልደታ ክፍለ ከተማ ሳርቤት እና ቫቲካን አካባቢ አባሎቻችንን እና ደጋፊዎቻችንን በማስተባበር ለወጣቶች ገንብተን ያጠናቀቅነውን የስፓርት ሜዳ ለአገልግሎት ክፍት በማድረግ በማስ ስፖርት የምርጫ ቅስቀሳ አካሂደናል።

ለከተማችን ወጣቶች በቅርበት በየሰፈሩ የስፖርት ማዘውተሪያዎችን በመገንባት ወጣቶች በአካል የጠነከሩ፣ በአዕምሮ የዳበሩ፣ ብቁ እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በመንግስት በጀት ብቻ ሳይሆን እንደ ፓርቲም የተለያዩ አካላትን በማስተባበር በትጋት እየሰራን እንገኛለን ።

ሃገር እየተንገባች ያለቸው ለወጣቶች ነው። ወጣቶችን ያለአግባብ መፈርጅ ሳይሆን ወጣቶች በእውቀታቸው፣ ባላቸው ተሰጥኦ መስራት እንዲችሉና ህልማቸውን እንዲያሳኩ በሁሉም መስክ ምቹ ሁኔታን መፍጠር ይጠበቃል።

ፓርቲያችን ብልጽግና የገባውን ቃል በተግባር ይፈፅማል፣ የወጣቶችን ተጠቃሚነት ያረጋግጣል።

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.